Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
  ሰንበት፣ የካቲት 25፣ 2015

የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ በሰሜን ህንድ ዩኒየን በፓታንኮት ውስጥ ላለው የጸሎት ቤት

ፓታንኮት በህንድ ፑንጃብ ግዛት ውስጥ ያለ ከተማ ነው። በምዕራብ ከፓኪስታን ጋር ስለምዋሰን የፑንጃብ፣ የሂማካል ፕራዴሽ እና የጃሙና ካሽሚር ግዛቶች የጉዞ ማዕከል ነው።

የተሃድሶው መልእክት እ.ኤ.አ. በ2015 እዚህ ደርሷል፣ እና አባላታችን ባለፉት አመታት አድጓል። በሰንበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርታችን ስርጭት ምክንያት፣ ብዙ ውድ አዳዲስ ነፍሳት የወቅቱን እውነት ለማወቅ በጉጉት ይፈልጋሉ።

እ.ኤ.አ. በ2011 የፓታንኮት ከተማና አካባቢ 159,909 ህዝብ ነበራት እንዲሁም ከነዚህም ማንበብና መጻፍ የሚችሉት 88.71% ናቸዉ። በሁለቱም በኩል በሺቫሊክ ክልል (የሂማላያስ ግርጌ ክፍል) እና በቻኪ ወንዝ ተከቧል። በፓታንኮት አቅራቢያ ያሉ ታዋቂ ቦታዎች ሻህፑር ካንዲ ለቱሪስቶች የተንጠለጠለ ማረፊያ ቤት እና ራንጂት ሳጋር ግድብ፣ በእስያ ከፍተኛው የስበት ኃይል (gravity dam) ግድብን ያካትታሉ። በአካባቢው ከሚገኙት ኢንዱስትሪዎች መካከል ወተት፣ ስንዴ፣ ሩዝ፣ ጨርቃጨርቅ፣ የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ ስኳር፣ ስታርች፣ ማዳበሪያ፣ ብስክሌት፣ ሳይንሳዊ መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የማሽን መሣሪያዎች እና የጥድ ዘይት ማምረቻ ይገኙበታል።

በፓታንኮት ውስጥ ያሉት ሃይማኖቶች ሂንዱይዝም 88.89%፣ ሲክሂዝም 8.01%፣ እና ክርስትና 1.73%፣ በመቀጠል እስልምና እና ሌሎች ሃይማኖቶች ናቸዉ።

በካንግራና ዳልሆውዚ በሚያማምሩ ተራሮች ግርጌ ላይ የምትገኝ፣ ቻኪ ወንዝ በአቅራቢያው የሚፈስስበት፣ ይህች ከተማ ብዙውን ጊዜ ወደ ጃሙ እና ካሽሚር፣ ዳልሃውዚ፣ ቻምባ፣ ካንግራ፣ ዳራምሻላ፣ ማክሊዮድጋንጅ፣ ጀዋላጂ፣ ቺንትፑርኒ እና ተጨማሪ ወደ ሂማላያ ተራሮች ከመሄዳቸዉ በፊት ለእንግዶች እንደ ማረፊያ ቦታ ትጠቅማለች። ብዙ የአጎራባች ክልሎች የገጠር ተማሪዎች ለትምህርት ወደ ፓታንኮት ይመጣሉ።

ፓታንኮት በባቡርና በመንገድ ከተቀረው የሕንድ ክፍል ጋር በጥሩ ሁኔታ የተገናኘ ነው፣ እና በፑንጃብ፣ በሂማሻል ፕራዴሽ፣ በዴሊ፣ በሃሪያና፣ በጃሙ እና በካሽሚር ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ከተሞች ጋር በሰፊው የግልና የህዝብ ዘርፍ የአውቶቡስ አገልግሎት የተገናኘ ነው። አስፈላጊ መዳረሻዎች ዴሊ፣ ማናሊ ቻንዲጋርህ፣ ጃሙ፣ ዳራምሻላ፣ ዳልሆውዚ እና አምሪሳር ይገኙበታል።

ስለዚህ፣ ልክ በየሱስ ዘመን እንደነበረው ቅፍርናሆም፣ ፓታንኮት ለመንገደኞች እንደ መስቀለኛ መንገድ ሆኖ ያገለግላል - እናም ወንጌልን ለመስበክ የሚያችል ሁነኛ አቅም አላት! እኛ መሬት የምንገዛበትና ቤተክርስትያን የምንገነባበት የራሳችን ሃብት የለንም። ስለዚህ በፓታንኮት ህንድ ለጌታ ሃውልት ለመስራት በትህትና ስጦታችሁን እንድትልኩልን የወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ድጋፍ እንፈልጋለን። “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል።” (2ኛ ቆሮንቶስ 9፡7) ስለዚህ በዚህ ተስፋ ጌታችን የሱስ እያንዳንዳችሁን በታላቅ በረከት እንዲባርክ እንጸልያለን።

ወንድሞችና እህቶች ከፓታንኮት ቤተክርስቲያን

 <<    >>