Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
  ሰንበት፣ ታህሳስ 29፣ 2015

የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ በሰሜን ካውካሰስ፣ ሩሲያ ውስጥ በአዲጂያ ውስጥ ላለው የትምህርትና የጤና ማእከል

የሩሲያ ግዛት 17,125,191 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (6,612,073 ስኩዌር ማይል) ሲሆን 146,780,000 ህዝብ ብዛት ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 111 ሚሊዮን ሩሲያውያን ናቸው። ከቀሪዎቹ 35 ሚሊዮን ውስጥ ከ180 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች ይገኙበታል። ዋናው ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ነው (42%) ቀጣዩ እስልምና (30%) ነው። ሌሎች ሃይማኖቶች ካቶሊካዊነት (3%)፣ የድሮ አማኞች (የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቅርንጫፍ) እና ፕሮቴስታንት (2%)፣ ቡዲዝም፣ የአይሁድ እምነት እና የግሪክ ካቶሊካዊነት (1%) ያካትታሉ።

ከ1925 ዓ.ም ጀምሮ የተሃድሶው መልእክት በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እዚህ ታውጇል። ብዙ ወንድሞች በእግዚአብሔር ቃል ምክንያት ታስረዋል። አንዳንዶች ለእውነት ሲሉ ሕይወታቸውን ከፍለዋል። በ1990ዎቹ ቤተ ክርስቲያናችን በነፃነት የመስበክ እድል ነበራት እናም ይህን አጋጣሚ በንቃት ተጠቅመዋል። በጁን 2018 የሩሲያ ህብረት ተደራጅቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በግልጽ የመስበክ እድላችን በጣም ውስን ስለነበር የካምፕ ስብሰባዎችን ለማካሄድና ለጤና ሚስዮናዊነት ሥራ የምንጠቀምበት ቦታ በተፈጥሮ ውስጥ እየፈለግን ነበር። በአስደናቂው የተራራማ መልክዓ ምድሮች እይታ በካውካሰስ ተራራማ ሥፍራ ላይ 5 ሄክታር የሚሆን ቦታ እንድንገዛ ጌታ ፈቅዶልናል። በተራራማው ክልል ውስጥ ውሃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የመሬቱ ዋጋ ዝቅተኛ ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታ ይህንን አክብዶ በእቅዱ ላይ ለመጠጥ ብቻ ሳይሆን ለኩሬም ጭምር የሚሆን የውሃ ምንጭ እንድናገኝ ረድቶናል። ለዚህ ታላቅ በረከቱ እናመሰግነዋለን! በ2019 ክረምት፣ በዚህ ምድር ላይ ምንም እንኳን መገንባት የቻልነዉ ለበጋ ስብሰባዎች ብቻ የሚያገለግሉ መጠለያዎችን፣ የመመገቢያ አዳራሽና ትንሽ ባለ ሁለት ክፍል ቤት ብቻ ቢሆንም የመጀመሪያውን የካምፕ ስብሰባ አደረግን። አንድ ዶክተር እዚያ የጤንነት ሴሚናር እንዲያካሂድ ተጋበዘ። በትንቢት መንፈስ ብርሃን መሰረትና ሁኔታዎቻችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለዚህ አላማ ተስማሚ የሆነ ቦታ ቢገነባ ለህክምና ሚስዮናዊ ስራ ትልቅ አቅም እናያለን።

በእግዚአብሔር ምህረትና ከመላው አለም ባሉ ወንድሞች እርዳታ በአካባቢያችን ያሉ ወንድሞቻችን በራሳቸው መክፈል የማይችሉትን ይህን ፕሮጀክት እንድናሳካ ጌታ እንደሚረዳን እናምናለን። ይህንን ፕሮጀክት በጸሎትና በገንዘብ መደገፍ የምትፈልጉ ሁሉ፤ ጌታ ይባርካችሁ።

ወንድሞችና እህቶች ከሩሲያ ዩኒየን

 <<    >>