Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 

መቅድም

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በዚህች ምድር ላይ ከ6,000 ለሚበልጡ ዓመታት የሠራውና ያቆየው በርግጥም አስደናቂና አስደማሚ ፍጥረት ናቸው። የታላቁ ፍጥረት ዘውድ ደግሞ በራሱ አምሳል የተፈጠረው የሰው ልጅ ነው! ይህ በዚች ፕላኔት ላይ ለመኖርና በእሷ ላይ የበላይነትን እንዲይዝ ታስቦ የተፈጠረ ፍጥረት ዘር ነው።

ለሰው ልጆች በተሰጠው የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ ምክንያት ይህ ዝርያ—ሆሞ ሳፒየንስ— ይህ መብት በአደራ ተሰጥቶታል። ከምንም በላይ ግን በምድር ላይ ግርማ ሞገስ ባለው ፈጣሪ ፊት ለዘላለም የመኖር እድል የተሰጠው ፍጥረት እርሱ ብቻ ነበር።

እንደ ማንኛውም ልዩ መብትና ኃላፊነት፣ ይህም ቅድመ ሁኔታዎች ያሉት ነበር። ጻድቅና መሐሪ የሆነዉ የዓለማት ፈጣሪ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በፊታችን በግልፅ አስቀምጦልን፤ የቃል ኪዳኑን ዝግጅት እንድንረዳ ከእርሱ ጋር እንድንወያይ ይጋብዘናል።

ስለዚህ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ በመላው ዓለም የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ተማሪዎች “ከፈጣሪያችን ጋር ማመዛዘን” የሚለውን ዋና ርዕስ ያጠናሉ። ይህም በቀጣይ ለአንድ ዓመት ሙሉ ከምንማረዉ “የእዉነት ዉድ ሀብቶች” ከሚለዉ ትልቅ ዋጋ ያላቸውን አስደናቂ የእውነት እንቁዎች በመረዳት ለዘለአለም ለመታጠቅ ከሚሆነዉ ትምህርት የመጀመሪያዉ ክፍል ነዉ። የሚድኑ ሁሉ በአምላክ ላይ ጥልቅ፣ እውነተኛ እምነትና በምድር ታሪክ ውስጥ የመጨረሻውን ሰዓት የሚያጋጥሙትን ፈታኝ ፈተናዎች እንኳን ሳይቀር የሚጸና የድል አድራጊ ክርስቲያናዊ ተሞክሮ ሊኖራቸው ይገባል።

የማሰብ ችሎታ ላላቸው ፍጥረታት የተነገረው ሃይማኖት እውነተኛ ስለመሆኑ ምክንያታዊ የሆኑ ማስረጃዎችን ያዘጋጃል፤ ምክንያቱም በልብና በባሕርይው ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛልና። የክርስቶስ ጸጋ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ይገለጣል። የተቀደሱ ነን የሚሉትን፣ የመንፈስ ፍሬዎች በህይወታችሁ ይገለጣሉን? የክርስቶስን የዋህነትና ትህትናን ትገልጣላችሁን፣ እንዲሁም በክርስቶስ ትምህርት ቤት በየቀኑ እየተማራችሁ መሆኑን፣ በህይወታችሁ ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነዉን የህይወቱን ምሳሌ በማንጸባረቅ እውነታውን ትገልጣላችሁን? ብለን እንጠይቅ።

ማናችንም ብንሆን ከሰማይ አምላክ ጋር ያለንን ግንኙነት ልናገኝ የምንችልበት ከሁሉ የተሻለው ማስረጃ ትእዛዛቱን መጠበቃችን ነው። በክርስቶስ ላይ ስላለን እምነት ከሁሉ የተሻለው ማረጋገጫ በራስ አለመተማመንና በእግዚአብሔር ላይ መታመን ነው። በክርስቶስ ለመኖራችን ብቸኛው አስተማማኝ ማረጋገጫ የእርሱን መልክ ማንጸባረቅ ነው። ይህን እስካደረግን ድረስ በእውነት እንደምንቀደስ እናረጋግጣለን፤ ምክንያቱም እውነት በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ምሳሌ ይሆናልና።”—Ye Shall Receive Power, p. 121.

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመታዘዝ ቢጥሩም ግን ጥቅት ሰላም ወይም ደስታ ብቻ የሚያገኙ ብዙዎች ናቸው። ይህ ተሞክሯቸዉ የተግባራዊ እምነት እጦት ውጤት ነው። በጨዋማ ምድር፣ በደረቅ ምድረ በዳ እንዳለ ይመላለሳሉ። ብዙ ሊጠይቁ እየቻሉ ጥቅት ብቻ ይጠይቃሉ፤ ምንም እንኳ ለእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ወሰን ባይኖረዉም።”—The Acts of the Apostles, p. 563.

በዚህ ሩብ ዓመት ሁላችንም በሰንበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንድንበለጽግና ሁሉንም አዋቂ ከሆነው ጋር በማገናዘብ እምነታችን እንዲናጠናከር ዘንድ ጸሎታችን ነው።

የጀነራል ኮንፈረንስ ሰንበት ትምህርት ክፍል መምሪያ

 <<    >>