Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
10ኛ ትምህርት ሰንበት፣ መጋቢት 2፣ 2023

"በእውነትህ ቀድሳቸው"

የመታሰቢያ ጥቅስ፡-“የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።” (ምሳ 4፡18)።

እራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ስንሰጥና ሙሉ በሙሉ ስናምን የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል። ሕሊና ከውግዘት ሊላቀቅ ይችላል። በደሙ ባለ እምነት ሁሉም በክርስቶስ የሱስ ፍፁም ሊሆኑ ይችላሉ። የማይቻሉ ነገሮችን ስላላስተናገድን እግዚአብሔር ይመስገን። እንቀደስ ይሆናል። የአምላክን ሞገስ እናገኝም ይሆናል። መጨነቅ ያለብን ክርስቶስና እግዚአብሔር ስለእኛ ስለሚያስቡት ነገር ሳይሆን እግዚአብሔር ተተኪያችን ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ስላለው አመለካከት ነው።”—Selected Messages, bk. 2, pp. 32, 33

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   The Acts of the Apostles, pp. 557–567. 

እሁድ የካቲት 26

1. መጽደቅ

ሀ. ኃጢአታችንን ስንናዘዝና ሕይወታችንን ለየሱስ አሳልፈን ስንሰጥ - በክርስቲያናዊ ልምምዳችን መጀመሪያ ላይም ሆነ በእያንዳንዱ ደረጃ - ከእግዚአብሔር ምን እናገኛለን? ሮሜ 3፡24-26

አዳም በኃጢአት ከመዉደቁ በፊት ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ ጻዲቅ ባሕርይን ማሳየት ይችል ነበር። ነገር ግን እርሱ ይህን ስላላደረገና ከእርሱ ወድቀትም የተነሳ የእኛ ተፈጥሮ በኃጢአት ስለጎደፈ ራሳንን ልናጸድቅ አልቻልም። ኃጢአተኞች፣ ቅድሰና የጎደለንና በኀጢአት የረከስን እንደመሆናችን፣ ቅዱሱን ሕግ በፍጽምና ልንታዘዘዉ አንችልም። የእግዚአብሔር ሕግ የሚጠይቀዉን ለማሟላት የራሳችን የሆነ ጽድቅ ባይኖረንም ክርስቶስ ግን ማምለጫዉን መንገድ አዘጋጀልን። እርሱ በኖረዉ ምድራዊ ሕይወቱ እኛ በምናልፈበት ፈተናና መከራ ዉስጥ አልፏል። ይሁንና ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት ኖረ። ስለዚህም ስለእኛ ሞቶ ኃጢአታችንን ለመዉሰድ ራሱን በመስጠት ጽድቁን አወረሰን። ራሳችሁን ለእርሱ ብትሰጡና እንደ አዳኛችሁ ብትቀበሉት የፈለገዉን ያህል ኃጢአተኛ የነበራችሁ ቢመስላችሁም፤ ስለ ራሱ ሲል እንደ ጽድቅ ይቆጥራችኋል። የክርስቶስ ባሕርይ በእናንተ ምትክ ተቆጥሮ በእግዚአብሔር አብ ፊት ምንም ኃጢአት እንዳልሠራ ሰዉ ሆናችሁ እንድትታዩ ያደርጋችኋል።”—ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ፣ ገጽ 58

ለ. ይህ ጉዞ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ምሳሌ 4:18ማርቆስ 13:13


ሰኞ የካቲት 27

2. የክርስትናን ጸጋዎች ማሻሻል

ሀ. ከይቅርታ/መጽደቅ በተጨማሪ እግዚአብሔር ሊሰጠን የሚፈልገው ሌላ ምንድ ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 7:1፤ ዕብራውያን 6:1ፊልጵስዩስ 3፡12-14

በዮሐንስ ሕይወት ውስጥ እንደሚታየው ዓይነት የባህሪ ለውጥ ከክርስቶስ ጋር የመገናኘት ውጤት ነው። በአንድ ግለሰብ ባህሪ ውስጥ ጉልህ ጉድለቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር በሚሆንበት ጊዜ፣ የመለኮታዊ ጸጋ ኃይል ይለውጠዋል እና ይቀድሰዋል። የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጨ ሲያይ የሚወደውን እርሱን እስኪመስል ድረስ ከክብር ወደ ክብር ይለወጣል።”—The Acts of the Apostles, p. 559.

ያለ ክርስቶስ ጸጋ፣ ኃጢአተኛው ተስፋ በሌለው ሁኔታ ውስጥ ነው። ለእሱ ምንም ማድረግ አይቻልም፤ ነገር ግን በመለኮታዊ ጸጋ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ኃይልን ለሰው ይሰጣል፣ እናም በአእምሮ፣ በልብና በባህሪይ ይሠራል። ኃጢአት በጥላቻ ተፈጥሮው የሚታወቀዉና በመጨረሻም ከነፍስ ቤተመቅደስ የሚባረረዉ የክርስቶስን ጸጋ ስንካፈል ነው።”—Selected Messages, bk. 1, p. 366

የሰውን ልብ ሊያድስና ነፍሳትን በክርስቶስ ፍቅር ሊሞላው የሚችል ከመለኮታዊ ሃይል በቀር ምንም ነገር የለም፣ ይህም ለሞተላቸው በፍቅር እራሱን ይገለጣል። የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዋህነት፣ ራስን መግዛት ነው። አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ሲለወጥ፣ አዲስ የሞራል ጣዕም ይቀርባል፣ አዲስ ተነሳሽነት ኃይል ይሰጠዋል፣ እና እግዚአብሔር የሚወዳቸውን ነገሮች ይወዳል፤ ሕይወቱ ከየሱስ ሕይወት ጋር በማይለወጥ የተስፋ ቃል የወርቅ ሰንሰለት የታሰረ ነውና። ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ እና የማይገለጽ ምስጋና ነፍስን ያበዛል፣ የተባረከ ሰው አንደበትም ይህ ይሆናል፣ “ተግሳጽህም ታላቅ አድርጎኛል” (መዝሙረ ዳዊት 18:35)።—Ibid., p. 336

ለ. ወደ መንግሥተ ሰማያት በሚወስደው መንገድ ላይ ለክርስቲያናዊ ጸጋዎች መሻሻል አንዳንድ ደረጃዎች ምንድናቸው? 2ኛ ጴጥሮስ 1:5-11

ምድርን ከሰማይ ጋር የሚያገናኘው መሰላል ክርስቶስ ነው። መሰረቱ በሰበአዊነቱ ውስጥ በምድር ላይ በጥብቅ ተተክሏል፤ ከላይ የመጨረሻዉ የመሰላሉ ደረጃ በመለኮቱ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ይደርሳል። የክርስቶስ ሰብአዊነት የወደቀውን የሰውን ልጅ አቅፎ፣ አምላክነቱ ደግሞ የእግዚአብሔር ዙፋን ይዟል። እኛም የዳንነዉ መሰላሉን በመውጣት፣ ክርስቶስን በመመልከት፣ ከክርስቶስ ጋር በመጣበቅ፣ ደረጃ በደረጃ ወደ ክርስቶስ ከፍታ በመውጣት ጥበብና ጽድቅ ቅድስናና ቤዛነትም ስለተደረግልን ነዉ።—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 147.


ማክሰኞ የካቲት 28

3. በእግዚአብሔር ቃል የሚገኝ ኃይል

ሀ. ክርስቲያናዊ እድገት ያለማቋረጥ እንዲቀጥል አምላክ አእምሮአችንን የሚያበራልን እንዴት ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4–6፤ መዝሙር 119:105ዘሌዋውያን 20:7፣ 8

የሰው ፈቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲተባበር ሁሉን ቻይ ይሆናል። በትእዛዙ የሚደረግ ማንኛውም ነገር በእርሱ ጥንካሬ ሊፈጸም ይችላል። ሁሉም ትዕዛዞቹ የሚቻሉ ናቸው።”—Christ’s Object Lessons, p. 333

የባህርይ ፍፁምነት ክርስቶስ ለእኛ በሆነው ላይ የተመሰረተ ነው። በአዳኛችን ትሩፋት ላይ የማያቋርጥ ጥገኛ ከሆንንና በእርሱ ፈለግ ከተጓዝን እንደ እርሱ ንፁህና እርኩሰት የሌለብን እንሆናለን።

አዳኛችን የማንንም ነፍስ መጥፋትን አይፈልግም። ለደቀ መዛሙርቱ አንድን ነገር እንዲያደርጉ ጸጋንና ጥንካሬን ሳይሰጣቸው ምላሽን ከእነርሱ አይጠብቅም። እርሱ በትእዛዙ መሠረት ሁሉንም የጸጋ ፍጽምናን ባያደርግ ኖሮ ፍጹማን እንዲሆኑ አይጠራቸውም ነበር። ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ስጦታ ለመስጠት ከምጓጉት ይልቅ እርሱን ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት የበለጠ ፈቃደኛ እንደሆነ አረጋግጦልናል።”—That I May Know Him, p. 130

ለ. ይህንን የክርስቲያኖች በቃሉ ኃይል በእውነት የማደግ ሂደት ምን እንላለን? ዮሐንስ 1:14፤ 17፡17።

“እውነት በህይወት ውስጥ ጸንቶ የሚኖር መርህ ሲሆን ነፍስ ዳግመኛ ትወለዳለች ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል። ይህ አዲስ ልደት ክርስቶስን እንደ እግዚአብሔር ቃል የመቀበል ውጤት ነው። በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ እውነቶች በልብ ላይ ሲደነቁ፣ አዳዲስ ሐሳቦች ይነሳሉ፣ እናም እስከ አሁን ተኝቶ የነበረው ኃይል ከእግዚአብሔር ጋር ለመተባበር ይነሳሳል።”—The Acts of the Apostles, p. 520.

የቤተክርስቲያን መቀደስ ከህዝቡ ጋር ባለው ግንኙነት ሁሉ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። ለዘላለም ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ መረጣቸው። ከራስ ታናሽነት ሁሉ ተለይተው ለእውነት በመታዘዝ ይቀደሱ ዘንድ ልጁን ስለ እነርሱ እንዲሞት አሳልፎ ሰጠ። ከእነርሱም የግል ሥራን፣ የግል እጅ መስጠትን (ራስን አሳልፎ መስጠትን) ይጠይቃል። በእርሱ አምነናል በሚሉት ሰዎች ሊከብሩት የሚችሉት በአምሳሉ እንደተፈጠሩና በመንፈሱ ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ብቻ ነው። ከዚያም፣ ለአዳኝ ምስክሮች፣ መለኮታዊ ጸጋ ያደረገላቸው ምን እንደሆነ ማሳወቅ ይችላሉ።”—Ibid., p. 559.


ረቡዕ የካቲት 29

4. የውሸት የይገባኛል ጥያቄዎች

ሀ. በመጽሐፍ ቅዱስ በዘመናት ሁሉ የነበሩትን የአምላክ ቅዱሳን ሰዎች ስንመለከት፣ የመጨረሻውን ድል ስለመቀዳጀት ምን መረዳት አለብን? 1ኛ ዮሃንስ 1:8፣ 10፤ ሮሜ 7:18ገላትያ 6፡14

ለዳንኤል የተሰጠው ክብር የመንግሥቱ መሪዎችን ቅናት ቀስቅሷል። ፕሬዚዳንቶቹ እና መኳንንቱ በእሱ ላይ ቅሬታ ለማቅረብ ፈለጉ። “ነገር ግን ምንም ምክንያት ወይም ስህተት ማግኘት አልቻሉም፤ የታመነ ነበርና ስህተትና በደል አልተገኘበትም” (ዳንኤል 6፡4)።

ለመላው ክርስቲያኖች ምን ትምህርት ቀርቧል? በዳንኤል ላይ የቅንዓት ዓይኖች ዕለት ዕለት ይታዩ ነበር። እይታቸው በጥላቻ ተሳለ፤ ነገር ግን በሕይወቱ ውስጥ አንድም ቃል ወይም ድርጊት ስህተት መስሎ ሊያገኙ አልቻሉም። እና አሁንም እርሱ ስለቅድስናዉ አልተናገረም፣ ነገር ግን እጅግ በጣም ጥሩ የሆነውን አደረገ—በታማኝነትና በመቀደስ ሕይወት ኖረ።”—The Sanctified Life, p. 42.

የዉሸት ቅድስና ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጪ ይመራል። ኃይማኖት ወደ ተረትነት ይወርዳል። ስሜቶች መስፈርቶች ይሆናሉ። ኃጢአት የሌለባቸው ነን ብለው በጽድቃቸው ሲመኩ፣ የመቀደስ ጥያቄ አቅራቢዎች ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግ ለመተላለፍ ነፃነት እንዳላቸውና ሥርዓቱን የሚታዘዙ ከጸጋ እንደወደቁ ያስተምራሉ። የይገባኛል ጥያቄዎችን ማቅረቡ ተቃውሟቸውን ያስነሳልና ቁጣንና ንቀትን ያነሳሳል። ስለዚህ ባህሪያቸው በግልጽ ይታያል፣ ምክንያቱም “ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል።” (ሮሜ 8፡7)።—Faith and Works, p. 53.

ለ. የመቀደስ አስፈላጊነት እናምናለን ማለት መዳናችንን በራሳችን ማግኘት አለብን ማለት ነውን? ዮሐንስ 14:15፤ 1ኛ ዮሐንስ 3:5፣ 6

ጽድቅ መነሻው እግዚአብሔርን በመምሰል ነው። ማንም ሰው በእግዚአብሔር ላይ እምነት ከሌለውና ከእርሱ ጋር ያለውን ግንኙነት ካላስጠበቀ ጻድቅ ሊሆን አይችልም። የሜዳ አበባ በአፈር ውስጥ ሥር እንዳለው፤ አየርን፣ ጤዛን፣ ዝናብንና ፀሐይን መቀበል እንዳለበት እንዲሁ የነፍስን ሕይወት የሚያገለግለውን ከእግዚአብሔር መቀበል አለብን። ትእዛዙን ለመታዘዝ ኃይልን የምንቀበለው የእሱ ባሕርይ ተካፋዮች በመሆን ብቻ ነው። ማንም ሰው ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛ፣ ልምድ ያለው ወይም ልምድ የሌለው፣ ህይወቱ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ካልተሰወረ በቀር በባልንጀሮቹ ፊት ንፁህ፣ ሃይለኛ ህይወትን በቋሚነት ሊጠብቅ አይችልም። በሰዎች መካከል ያለው እንቅስቃሴ በጨመረ መጠን የልብ ቁርኝት ከእግዚአብሔር ጋር መቀራረብ ይኖርበታል።”—Testimonies for the Church, vol. 7, p. 194


ሐሙስ የካቲት 30

5. ስለ መቀደስስ ምን ማለት ይቻላል?

ሀ. መቀደስ—በክርስቲያናዊ ባሕርይ ማደግ—በተለይ ይህ እየተፈጸመ ላለበት ግለሰብ ይታወቀዋልን? ማርቆስ 4:26-29 ለሌሎችስ?

ያልተጠና፣ አዉቀዉ የማያደርጉት (unconscious) የቅድስኛ ህይወት ተጽእኖ ለክርስትና ጥቅም ሊሰጥ የሚችል እጅግ አሳማኝ ስብከት ነው። ክርክር፣ መልስ በማይሰጥበት ጊዜ እንኳን፣ ተቃውሞን ብቻ ሊያስነሳ ይችላል፤ ነገር ግን አምላካዊ ምሳሌነት ሙሉ በሙሉ ለመቃወም የማይቻል ኃይል አለው።”—The Acts of the Apostles, p. 511

ለ. ይህ እድገት ቀጣይነት ያለው መሆኑንና በእድገታችንና በስኬቶቻችን ረክተን ማረፍ እንደማንችል የሚያሳየው ምንድን ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 15:31፤ ማቴዎስ 10:22ፊልጵስዩስ 3፡12-16

እግዚአብሔር ሁሉም ወንድና ሴት ልጆቹ ደስተኛ፣ ሰላማዊና ታዛዥ እንዲሆኑ ይፈልጋል። . . . በእምነት እያንዳንዱ የባሕርይ ጉድለት ይሞላል፣ እያንዳንዱ ቆሻሻ ይጸዳል፣ እያንዳንዱ ስህተት ይስተካከላል፣ እንዲሁም እያንዳንዱ መልካም ችሎታ ይጎለብታል።—The Acts of the Apostles, p. 564.

መቀደስ የአንድ አፍታ፣ የአንድ ሰዓት፣ የአንድ ቀን ስራ አይደለም፣ ነገር ግን የህይወት ዘመን ስራ ነው። በደስተኛ የስሜት በመዋኘት ሳይሆን ያለማቋረጥ ለኃጢአት በመሞትና ለክርስቶስ ያለማቋረጥ የመኖር ውጤት ነው። በደካማ፣ አልፎ አልፎ በሚደረጉ ጥረቶች ስህተቶችን ማስተካከልም ሆነ ማሻሻያዎችን ማድረግ አይቻልም። የምናሸንፈው በረጅም፣ ጽናት ባለው ጥረት፣ በከባድ ተግሣጽና በከባድ ግጭት ብቻ ነው። ግጭታችን በሚቀጥለው ጊዜ ምን ያህል ጠንካራ እንደሚሆን አንድ ቀን አናውቅም። ሰይጣን በሚነግሥበት ጊዜ ሁሉ፣ ራሳችንን በመካድ ኃጢአትን ለማሸነፍ ጥረት እናደርጋለን። ሕይወት እስካለች ድረስ፣ መቆሚያ ቦታ አይኖርም፣ ሙሉ በሙሉ ደረስኩበት የምንልበት ነጥብ የለም። መቀደስ የዕድሜ ልክ መታዘዝ ውጤት ነው።”—Ibid., pp. 560, 561.


አርብ መጋቢት 1

የግል የግምገማ ጥያቄዎች

1. እያንዳንዱን የጽድቅ ቅጽበትን በተመለከተ በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ዓይነት አያያዝ ይኖረናል?

2. አምላክ ለእኛ ያለው ፍላጎት ከይቅርታ በላይ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው?

3. የመለወጥ ምስጢር ምንድን ነው?

4. የውሸት መቀደስ ወደ ምን ይመራናል?

5. ቅድስና ቀጣይነት ያለው የማደግ ሕይወትን እንደሚጨምር እንዴት እናውቃለን?

 <<    >>