Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
  ሰንበት፣ ጥር 27፣ 2015

የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ ለአለም የአደጋ እፎይታ

በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጥሮ አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደጋጋሚና ከባድ እየሆኑ መጥተዋል። እነዚህም——የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ሱናሚዎች፣ አውሎ ነፋሶች፣ ማዕበሎች፣ ከፍተኛ አውሎ ነፋሶች፣ ጎርፍና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎችን የሚያካትቱ ቢሆንም በዚህ ብቻ የተወሰኑ አይደሉም። ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል። . . . ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራችው ይዞራል።” (ኢዮብ 37፡9-13)።

ሁሉን ቻይ የሆነው የዚህች ውብ ፕላኔትና የፈጠራቸው ፍጥረታት የመጨረሻ ጥቅሞችን በአእምሮው ይይዛል - ዛሬም ፣ ብዙ እንግዳ እና ከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ከነፍሳት ዋና ጠላት ጦር መሳሪያ ሆነዉ እየመጡ ነው።

“[ሰይጣን] በሽታዎቻቸውን ሁሉ መፈወስ የሚችል ታላቅ ሐኪም እንደሆነ አድርጎ ለሰው ልጆች ቢታይም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች እስኪወድሙና ምድረበዳ እስኪሆኑ ድረስ በሽታንና ጥፋትን ያመጣል። አሁን እንኳ፣ በዚህች ሰዓት በሥራ ላይ ነው። በየብስና በባህር አደጋዎችና ጥፋቶች፣ በታላላቅ አውዳሚ እሳቶች፣ በኃይለኛ ነፋስ (tornedo)ና በረዶ፣ በውሽንፍር፣ በጎርፎች፣ በአውሎ ነፋሳት፣ በውኃ ማዕበል፣ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በእያንዳንዱ ሥፍራ በሺህ አይነት መንገድ ሰይጣን ኃይሉን እየተጠቀመ ነው። እየጎመራ ያለውን አዝመራ ጠራርጎ ይወስደውና ረሃብና ጭንቀት ይከተላል። ለአየሩ ገዳይ ብክለት ይሰጥና በሺዎች የሚቆጠሩ በወረርሽኙ ይረግፋሉ። እነዚህ ጥፋቶች የበለጠ ተደጋጋሚና አስከፊ እየሆኑ የሚሄዱ ናቸው። ውድመት በሰውና በእንስሳ ላይ ይሆናል። “ምድርም አለቀሰች ረገፈችም። ታላላቆች ደከሙ። ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች፤ ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ስርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና” [ኢሳ 24÷4፣5]።”—The Great Controversy, pp. 589, 590.

ምንም ይሁን ምን፣ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለሚደርሰው ከፍተኛ ሰብዓዊ ሥቃይ የአምላክ ልጆች ምላሽ እንዲሰጡ የተጠሩት እንዴት ነው?

ጌታ በምድር ላይ በተገኘበት ቦታ ሁሉ መከራን ለማስታገስ የራሱን ምሳሌ እንድንከተል አዞናል። የተፈጥሮ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ለሕይወት የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች በድንገት ይጠፋሉ፣ ስለዚህ በማንኛውም ቦታ መርዳት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው። ለአለም የአደጋ እፎይታ ያደረጋችሁት ለጋስ ሥጦታ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል።

በቅድሚያ እናመሰግናለን!

ወንድሞቻችሁ ከጀነራል ኮንፈራንስ

 <<    >>