Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
11ኛ ትምህርት ሰንበት፣ መጋቢት 9፣ 2015

አሮጌዉ ኪዳን

የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ጌታ። ዕብራዊያን 8፡8

እግዚአብሔር በሰፈሩ ውስጥ የሆነውን አየ። ሰዎቹ፣ መለኮታዊው ክብር ሳይነሳ ገና በሲና ተራራ ላይ እያለ፣ ለሰይጣን ፈተናዎች እንደተገዙ እና ሊታዘዙት ቃል በገቡለት አገዛዝ ላይ እያሴሩ እንደሆነ ተመልክቷል።”—The Youth’s Instructor, November 21, 1901

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   አበዉ እና ነቢያት፣ገጽ 370–373። 

እሁድ መጋቢት 3

1. ባርነት አእምሮን ግራ ያጋባል

ሀ. እስራኤላውያን ለተወሰኑ ዓመታት ያሳለፉት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ይህ ሁኔታ ስለ አምላክና ስለ ሕጎቹ ያላቸውን እውቀት የጎዳው እንዴት ነው? ዘጸአት 20:1፣ 2፤ ዘዳግም 5:15

ዕብራዊያኑ በግብጽ የባርነት ዘመናቸዉ ስለ እግዚአብሔር የነበራቸዉ እዉቀትና የአብርሃምን ኪዳን መርሆች በከፍተኛ መጠን አጥተዉ ነበር። እግዚአብሔር ከግብጽ ሲያወጣቸዉ ይወዱትና ይተማመኑት ዘንድ ኃይሉንና ምህረቱን ሊገልጽላቸዉ ተመኘ። ግብጻዊያዉኑ ወደ እነርሱ እየገፉ ሲመጡና ማምለጫ መንገድ ሲጠፋ፤ ረዳት አልባነታቸዉን በመመለከት የመለኮትን ጣልቃ ገብነት ያስተዉሉ ዘንድ ቁልቁል ወደ ቀይ ባሕር ካመጣቸዉ በኋላ ከአሳዳጆቻቸዉ እጅ አዳናቸዉ። እስራኤላዊያን በታደጋቸዉ አምላካዊ ኃይል ብርቱ መተማመን ይዘዉ እግዚአብሔርን ወደዱት፣ ታላቅ ምስጋናም ሰጡት፤ የግዞት ዘመናቸዉን አክትሞ የራሱ ሕዝብ አድርጓቸዋልና።

ነገር ግን አሁንም ታላቅ እዉነት አዕምሯቸዉ ላይ ተጸዕኖ እንዲኖረዉ ይፈለግ ነበር። በጣዖት አምላኪያንና በእርክስና ዉስጥ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር አብረዉ በመኖራቸዉ የገዛ ልባቸዉ በማያባራ ኃጢአት ዉስጥ ተዘፍቆ ነበር። የእግዚአብሔርን ሕግ ለመታዘዝና አዳኙ እንደሚያስፈልጋቸዉ ያሳት የነበረዉ ተነሳሽነት እጅግ ደካማ በመሆኑ ስለ እግዚአብሔር ቅድስን እዉነተኛዉ ግንዛቤ አልነበራቸዉም። በመሆኑም እነዚህን ሁሉ መማር የግድ ነበር።”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 420 (1)

ለ. የሕጉን ቅድስናና ጻዲቅነት ይረዱ ዘንድ እግዚአብሔር ወዴት አመጣቸው? ዘጸአት 19:1፣ 5፣ 6


ሰኞ መጋቢት 4

2. የኃጢአት ክፋት

ሀ. እስራኤላውያን አምላክ ሲነግራቸው ሕጉን ከተረዱ በኋላ ለበረከት ተስፋዎች ምን ምላሽ ሰጡ? ዘጸአት 19:8፤ 24፡3።

ያለክርስቶስ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ የማይችሉት እነዚህ ሕዝቦች የገዛ ልባቸዉን ኃጢአተኝነት ሳያስተዉሉ ከእግዚአብሔር ጋር ኪዳን ሊገቡ ተዘጋጁ። የገዛ ጽድቃቸዉን ለማጽናት እንደሚችሉ ሆኖ ስለተሰማቸዉ “እግዚአብሔር ያዉን ሁሉ እናደርጋለን፤ እንታዘዛለን አሉ” (ዘጸ. 24፡7)። ሕጉ በአስፈሪ ግርማ ሲታወጅ አማኝ ሆነዉ ከተራራዉ ፊት በፍርሃት ቢንቀጠቀጡም፤ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ኪዳን አፍርሰዉ በጥጃ ምስል ለተሠራዉ ጣኦት አጎንብሰዉ ለመስገድ የወሰደባቸዉ ጥቅት ሳምንታት ብቻ ነበሩ። የገቡትን ኪዳን በማፍረሳቸዉ ዳግመኛ የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን ብለዉ ተስፋ ማድረግ አልቻሉም። አሁን ግን ኃጢአተኝነታቸዉን በመመለከትና ይቅርታ እንደሚያሻቸዉ በማሰብ በአብርሃማዊዉ ኪዳን ተገልጾ ነገር ግን በመስዋዕታዊ ስርዓት የተሸፈነዉ አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተሰማቸዉ። አሁን በእምነት በፍቅር ከኀጢአት ግዞት ወደ አዳናቸዉ አምላክ ዞሩ። በዚህ ወቅት በአዲሱ ኪዳን በረከቶች ደስ ለመሰኘትና ምስጋና ለማቅረብ ዝግጁ ነበሩ።”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 420፣ 421 (1)

ለ. የዚህ ቃል ኪዳን ውሎች ምን ነበሩ? ዘዳግም 27:26ሕዝቅኤል 20:11ዘሌዋውያን 18:5

ሐ. ከተፈጥሯዊ ሁኔታችን ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ ምን ሊረዱት አልቻሉም? ኤርምያስ 17:9ኢሳይያስ 1:5፣ 6፤ 64፡6።

“ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አለ “እርሱ ቅዱስ አምላክ ነዉ … አመጻችሁን ወይም ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።” ማንኛዉም ዘላቂ ተሃዲሶ ከመምጣቱ አስቀድሞ ሰዎች በሥጋዊ አስተሳሰብ ተገፋፍተዉ እግዚአብሔርን መታዘዝ እንደማይችሉ ሊሰማቸዉ ይገባል። ሕጉን በመጣሳቸዉ እንደ ተላላፊ ስለኮነናቸዉ፤ አንዳችም ማምለጫ መንገድ አልተወላቸዉም ነበር። በራሳቸዉ ጥንካሬና ጽድቅ በመታመናቸዉ ለኀጢአታቸዉ ይቅርታ ለማግኘት ለማግኘት አልተቻላቸዉም። ቅዱሱ አምላካዊ ሕግ የሚጠይቀዉን ባለማሟላታቸዉ እግዚአብሔርን ለማገልገል የገቡት ቃል ከንቱ ነበር። ደህንነት ያገኙ ዘንድ በራሳቸዉ ጥረት ምላሽ ከመስጠት በመቆጠብ፤ ቃል በተገባዉ አዳኝ መታመን ነበረባቸዉ። ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።”—Ibid., p. 171፣ 172 (2)


ማክሰኞ መጋቢት 5

3. ቃል ኪዳኑን ማጽደቅ

ሀ. ሙሴ ሕጉን ሁሉንም የእርግማንና የበረከት ሁኔታዎች ካነበበ በኋላ እስራኤላውያን ያለማቋረጥ ምላሽ የሰጡት እንዴት ነው? ዘጸአት 24፡7

የሰዎች አእምሮ የታወረና በባርነት የተዋረደ ስለነበረ፣ የእግዚአብሔርን አስሩ ትእዛዛት መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማስተዋል ዝግጁ አልነበረም። የሕጉን ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ እንዲረዱና ተፈፃሚ እንዲያደርጉ፣ የአስሩ ትእዛዛት መመሪያዎችን የሚያሳዩና የሚያስተገብሩ ተጨማሪ መመሪያዎች ተሰጥተዋል። ከየአስሩ ትእዛዛት በተለየ መልኩ እነዚህ ለሙሴ በግል ተሰጥተዋል፤ እሱም ለሕዝቡ እንዲነግራቸው ተደርጓል።”——Fundamentals of Christian Education, p. 506.

ሙሴ የጻፈው አሥርቱን ትእዛዛት ሳይሆን የማይታዘዙ ከሆነ የሚደርስባቸዉን ፍርድ እና ቅድመ ሁኔታዎችን የሚታዘዙት የሚጠብቃቸዉን የተስፋ ኪዳንን ነው። ይህንንም ለሕዝቡ አነበበ፣ እናም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ እንታዘዛለን በማለት ተስማሙ። ሙሴም ኪዳናቸውን በመጽሐፍ ጻፈ፥ ስለ ሕዝቡም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ። የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወሰደ፥ በሕዝቡም ፊት አነበበ። እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም አሉ። ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፥ እንዲህም አለ፡- “እነሆ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባዉ የቃል ኪዳኑ ደም ይህ ነዉ።” ሕዝቡም ጌታ የተናገረውን ሁሉ ለማድረግ እና ለመታዘዝ የገቡትን ቃል ኪዳን ደገሙት።”—The Spirit of Prophecy, vol. 1, p. 240.

ለ. እንዲህ ዓይነቱ ስምምነት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማሳየት ወዲያውኑ ምን ተደረገ? ዘጸአት 24:6፣ 8

ስለዚህ ህዝቡ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸምና ለመታዘዝ ለጌታ የገቡትን ቃል ኪዳን አፀደቁ።”—The Signs of the Times, May 6, 1880

እዚህ ህዝቡ የቃል ኪዳኑን ቅድመ ሁኔታዎች ተቀበሉ። በእግዚአብሔርና በየሱስ ክርስቶስ አማኝ ሁሉ መካከል የተደረገውን ቃል ኪዳን የሚያሳይ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ገቡ። ቅድመ ሁኔታዎቹ በህዝቡ ፊት በግልፅ ተቀምጠዋል። ቅድመ ሁኔታዎቹን በተሳሳተ መንገድ እንዲረዱ አልተተዉም ነበር። በተሰጡት ሁኔታዎች ሁሉ መስማማታቸዉን ወይም አለመስማማታቸዉን እንዲወስኑ በተጠየቁ ጊዜ ሁሉንም ግዴታዎች ለመታዘዝ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል። ሁሉም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመታዘዝ ተስማምተው ነበር። ሕጉን ለመታዘዝ በቃል ኪዳን ውስጥ ምን ያህል እንደተደረገ እንዲያውቁ የሕጉ መርሆዎች አሁን ተለይተዋል፤ ልዩ ቅጣት የተጣለባቸውን የሕግ ዝርዝሮችም ተቀበሉ።”—Manuscript Releases, vol. 1, p. 114


ረቡዕ መጋቢት 6

4. የጠፋዉ ትውልድ

ሀ. አብዛኞቹ የእስራኤል ብሔር ራሳቸውን ማዳን አለመቻላቸውንና ያለ መለኮታዊ እርዳታ ሕጉን መጠበቅ አለመቻላቸውን ስላልተገነዘቡ ምን አጋጠማቸው? ዘኍልቍ 26፡63–65።

“እኛ በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸዉ ነገሮች በሙሉ በኃጢአት የረከሱ ናቸዉ።”—Christ’s Object Lessons, p. 311

ኒቆዲሞስ መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ንስሃ መግባት፣ ስለጥምቀትና በመንፈስ ቅዱስ ስለሚያጠምቀዉ ሰዉ ሲሰብክ ሰምቶ ነበር። ኒቆዲሞስ ራሱ አይሁዶች መንፈሳዊ ድህነት እንዳጠቃቸዉ ማለትም የቀኖናዊነትና የዓለማዊ ምኞት ተገዥ መሆናቸዉ ይሰማዉ ነበር። መሲሑ ሲመጣ ሁኔታዎች ይሻሻላሉ የሚል ተሰፋ ነበረዉ። ነገር ግን ልብን የሚመረምረዉ የመጥምቁ መልዕክት የኃጢአተኛነት ስሜት እንዲኖረዉ አላደረገም። ጥንቁቅ ፈሪሳዊ ስለነበረ በጥሩ ሥራዉ ይኮራ ነበር። ስለ በጎ አድራጎቱና ቤተ መቅደሱን ለመርዳት በሚያደርገዉ ልግስና በሰፊዉ የታወቀ ስለነበረ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞግስን እንደሚያገኝ ጥርጣሬ አልነበረዉም። እርሱ አሁን ባለበት ሁኔታ ሊያየዉ ብቃት የሌለዉ ፍጹም የሆነ መንግሥት ይኖራል የሚለዉ አስተሳሰብ አስደነገጠዉ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 157.

ለ. ችግሩ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ወይንስ በዚህ “አሮጌ” ቃል ኪዳን ውስጥ ባሉት ሰዎች? ዕብራውያን 8፡8

“ተፈጥሮአዊ (የዉርስ) ክርስቲያን! ይህ አሳሳች ሃሳብ ለብዙዎችን እንደ የራስ የጽድቅ ልብስ ሆኖ አገልግሏል፣ እና ብዙዎች ስለ እርሱ፣ ስለ ልምምዱ፣ ስለ መከራዎቹ፣ ስለ እራስ የመካድ እና ስለ ራስን የመስዋዕትነት ህይወቱ ምንም እዉቀቱ ሳይኖራቸዉ በክርስቶስ ተስፋ እንዲያደርጉ አድርጓቸዋል። በብዙ የሚመታደቁበት ጽድቃቸው እንደ መርገም (እርኩሰት) ጨርቅ ብቻ ነው። የተወደደው መምህር ክርስቶስ፡- “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” አዎን፣ በክፉም በመልካምም እርሱን ተከተሉት። በጣም ለተቸገሩትና ወዳጅ ለሌላቸዉን ወዳጅ በመሆን እርሱን ተከተሉት።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 177, 178

ባለጠጋና ሀብታም እንደሆኑ የሚሰማቸዉ ራቁትነትና ድህነት በምንድር ነው?—ይህ የክርስቶስ ጽድቅ እጦት ነው። በራሳቸው ፅድቅ የረከሰ ጨርቅ እንደለበሱ ተገልጸዋል፣ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የክርስቶስን ጽድቅ እንደለበሱ ራሳቸውን ያሞካሻሉ። ከዚህ የበለጠ ማታለል ሊኖር ይችላልን? በነቢዩ እንደተገለጸዉ ልባቸው በእርኩስትና በክፋት ተሞልቶ እያለ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እኛ ነን” (ኤርምያስ 7:4ን ተመልከት) እያሉ ይጮሃሉ።-This Day With God, p. 228.


ሐሙስ መጋቢት 7

5. ሌላ ቃል ኪዳን ያስፈልጋል

ሀ. አሮጌው ኪዳን በጣም ተስፋ ስለሌለው፣ በብሉይ ኪዳን ዘመን ለሚኖሩት ተስፋ የሚሰጥ ብቸኛው የተስፋ ቃል ምንድን ነው? ኤርምያስ 31:31-33

በክርስቶስ በማመን ለህግ ሁሉ መታዘዝ ተችሏል።

የባርነት መንፈስ የሚመነጨው በህጋዊ ሀይማኖት መሰረት ለመኖር በመፈለግ፣ የህግ ጥያቄዎችን በራሳችን ሀይል ለማሟላት በመታገል ነው። ለእኛ ተስፋ ያለን በአብርሃም ቃል ኪዳን ሥር ስንሆን ብቻ ነው እርሱም በክርስቶስ የሱስ በማመን የሚገኘው የጸጋ ቃል ኪዳን ነው። ለአብርሃም የተሰበከለት፣ በእርሱም ተስፋ የነበረው ወንጌል ዛሬ የተሰበከልን፣ በእርሱም ተስፋ ያለንበት ወንጌል ነው። አብራሃም የሱስን ተመልክቶ ነበር፣ እርሱም ደግሞ የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ ነዉ።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, p. 1077..

ለ. በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እነዚህን የመለኮታዊ እርዳታ ተስፋዎች የተቀበሉ ጀግኖችን ጥቀስ። ዕብራውያን 11:4-32

የእምነት ጀግኖች ከዘመን እስከ ዘመን ለእግዚአብሔር ባላቸው ታማኝነት ተለይተው ይታወቃሉ፣ እናም ብርሃናቸው በጨለማ ላሉት እንዲበራ በዓለም ፊት ጎልቶ ቀርቧል። ዳንኤል እና ሦስቱ አጋሮቹ የክርስቲያን ጀግንነት ምሳሌዎች ናቸው። . . . አምላክ በፍጹም ዓላማ እሱን ለሚያገለግሉት ሰዎች ምን እንደሚያደርግላቸው በባቢሎን አደባባይ ካገኙት ተሞክሮ እንማራለን።”—My Life Today, p. 68


አርብ መጋቢት 8

የግል የግምገማ ጥያቄዎች

1. የመለኮታዊውን የሥነ ምግባር ሕግ ትክክለኛ ትርጉም መረዳት ባለመቻላችን የዕብራውያንን ተሞክሮ የምንከተለው እንዴት ነው?

2. ሊፈጽሙት የማይችሏቸውን ቃል ኪዳን ወዲያውኑ የገቡት ለምንድን ነው?

3. በዛሬው ጊዜ ለአምላክ ተመሳሳይ ኪዳኖችን እንድንሰጥ በቀላሉ የምንመራው እንዴት ነው?

4. በቀሪው የእስራኤል ታሪክ ውስጥ ምን እየተፈጸመ ነው?

5. ብሄራዊ ክህደት ለእምነታችን መንገጫገጭ ሰበብ እንደማይሆን የሚያሳዩ ምን ምሳሌዎች አሉን?

 <<    >>