Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
3ኛ ትምህርት ሰንበት፣ ጥር 13፣ 2015

እሳታማ እባቦች

የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” (ማቴ 11፡28-30)።

የእግዚአብሔር ልጅነት ለእኛ ሁሉም ነገር ነው። ነፍሳችንን ከክርስቶስ ጋር፣ በክርስቶስ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያቆራኘው የወርቅ ሰንሰለት ነው። ይህ የእኛ ጥናት ይሆናል።”—Selected Messages, bk. 1, p. 244.

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 48፣ 49፣ 114–123። 

እሁድ ጥር 7

1. የአብርሃም ዘር

ሀ. በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከባድ አደገኛ አመለካከት ግለጽ። የዮሐንስ ወንጌል 8፡33

ለ. የኃጢአት ባሪያዎች እንድንሆን የሚያደርገን ምንድን ነው? ዮሐንስ 8:34፣ 39–44

ፈሪሳውያን የአብርሃም ልጆች ነን ባዮች ነበሩ። የሱስ ግን ያ መብት ሊኖራቸዉ የሚችለዉ የአብርሃምን ሥራ ሲሠሩ ብቻ እንደሆነ ነገራቸዉ። እዉነተኛ የአብርሃም ልጆች የሆኑ ሁሉ እርሱ እንዳደረገዉ ለእግዚአብሔር ታዛዥ የሆነ ሕይወት ይኖራሉ እንጂ ከእግዚአብሔረ የተሰጠዉን እዉነት የሚናገርን ሰዉ ሕይወት ለማጥፋት አይሞክሩም። እነዚያ የኦሪት ሕግ ሊቃዉንት በየሱስ ላይ ሲያሴሩ የአብርሃምን ሥራ መሥራታቸዉ አልነበረም። በትዉልድ ብቻ የአብርሃም ዘር መሆን ምንም ፋይዳ የለዉም። እነዚህ ሰዎች የአብርሃም መንፈስ እንዲያድርባቸዉና የእርሱንም ሥራ እንድሠሩ የሚያደርጋቸዉ ከእርሱ ጋር የሚያስተሳስራቸዉ መንፈሳዊ ግንኙነት እስካልኖራቸዉ ድረስ የአብርሃም ልጆች ሊሆኑ አይችሉም።”— የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 481

ሐ. ከዚህ የጨካኝ ጌታ ግፍ እንዴት መታደግ ይቻላል? ዮሐንስ 8:32፣ 36፤ ገላ 3፡29


ሰኞ ጥር 8

2. “ማወቅ” ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ጲላጦስ በፍርድ አዳራሽ ውስጥ ምን በጣም አስፈላጊ ጥያቄ አቀረበ? ዮሐንስ 18፡38 (የመጀመሪያ ክፍል)። የአዳኙን ምላሽ ለማዳመጥ ለአፍታ ጊዜ ቢሰጥ ኖሮ ምን መልስ ይሰጠው ነበር? ዮሐ. 14፡6

ጲላጦስ እውነቱን የማወቅ ፍላጎት ነበረው። ግራ ቢጋባም የሱስ የተናገራቸዉን ቃላት በጉጉት በማዳመጥ እዉነትን ለማወቅና ይህን እዉነት እንዴት ሊያገኘዉ እንደሚችል በነበረዉ ፍላጎት “እዉነት ምንድነዉ” ሲል ጠየቀ። ነገር ግን ለጥያቄዉ መልስ ለመስማት አልተጠባበቀም። ካህናቱ ፈጣን ዉሳኔ እንዲሰጣቸዉ ይጮኹ ስለነበረ ከዉጭ ይሰማ የነበረዉ ሁካታ የወቅቱን ሁኔታ አስታወሰዉ። ስለዚህ አይሁዳዊያዉኑ ወደነበሩበት ወጥቶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም” ሲል በአጽንኦት ተናገረ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 768.

ለ. አንድ ሰው እግዚአብሔርን ሳያውቅ ቃሉን የሚያጠና ከሆነ ምን ሊሆን እንደሚችል አስረዳ። ማርቆስ 12:24፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:7

ሰዱቃውያን ሰዎች ሁሉ ቅዱሳት መጻሕፍትን አጥብቀው በመጠበቃቸው ራሳቸውን አመሰገኑ። የሱስ ግን ትክክለኛ ትርጉማቸውን እንደማያውቁ አሳይቷል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 605.

ሐ. የወደቀው ተፈጥሮአችን ወደማይፈልገው ሰው እንዴት መቅረብ ይቻላል? ዮሐንስ 12:32፤ 8:28፤ ማቴዎስ 11:28-30

ሕግ በሕዝብ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ፣ የእውነት መምህር ወደሆነዉ በተስፋ ቃል ቀስተ ደመና ባሸበረቀዉ ዙፋን ላይ ወደ ተቀመጠዉ፣ ወደ ክርስቶስ ጽድቅ ያመልክት። የሕግ ክብር ክርስቶስ ነው፤ እርሱ ሕግን ሊያጎላና ሊያከብር መጣ። ምህረትና እውነት በክርስቶስ አንድ ላይ እንደተገናኙ እና ቅንነትና ሰላምም እርስ በርሳቸው እንደተቃቀፉ ግልጽ አድርጉ። ንስሐህንና ውዳሴህን ለእግዚአብሔር ስታቀርብ፣ ክርስቲያናዊ ባሕርይን ፍጹም አድርገህ ክርስቶስን ለዓለም የምትወክለው ወደ ዙፋኑ ስትመለከት ነዉ። እናንተ በክርስቶስ ስትኖሩ ክርስቶስም በእናንተ ይኖራል፤ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ይኖራችኋል።

በክርስቶስና በሚደንቅ ፍቅሩ ላይ ያለማቋረጥ ማሰላሰል ያስፈልገናል። አእምሮን ወደ የሱስ በመምራት፣ በእርሱ ላይ መጠማጠም አለብን። በእያንዳንዱ ንግግር ውስጥ በመለኮታዊ ባህሪያት ላይ ማትኮር አለብን።”—The Ellen G. White 1888 Ma-terials, p. 730

የመለኮታዊ-ሰበአዊዉን ባህሪይ በጥንቃቄ አጥኑና ያለማቋረጥ ጠይቁ፡- “የሱስ በእኔ ምትክ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?””—The Ministry of Healing, p. 491


ማክሰኞ ጥር 9

3. በበረሃ ውስጥ እባቦች

ሀ. እግዚአብሔር በምድረ በዳ በመርዛማ እባቦች ለተነደፉት ምን መድኃኒት አዘጋጀላቸው? ፈውስ እንዲከሰት ምን አስፈለገ? ዘኍልቍ 21፡6–9

በመለኮታዊ ኃይል [የእስራኤል ልጆች] ተጠብቀው ስለነበር በተከታታይ የከበቧቸዉን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን አደጋዎች አላስተዋሉም። ምስጋና ቢስና የማያምን መንፈስ የተቆራኛቸዉ እሥራኤላዊያን ሞት ተመኙ። ጌታም የተመኙትን ሞት ፈቀደላቸዉ። በምድረ በዳዉ እጅግ የሚፈሩ ኃይለኛ ተናዳፊ እባቦች ነበሩ። በእነዚህ እባቦች የተነደፈ ሰዉነቱ ያብጥና በቅጽበት ይሞታል። ሕዝቡን ከአደጋ የሚታደገዉ አማላካዊዉ እጅ ከእነርሱ ላይ በተነሳ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሕዝብ በተናዳፊዎቹ እባቦች ጥቃት ደረሰበት።. . .

ሙሴ በሕይወት ያለዉን የሚመስል የናስ እባብ እንዲሠራና በሕዝቡ መካከል ለሁሉም በሚታይ ቦታ እንዲሰቅለዉ በመለኮት ታዝዞ ነበር። በእባቡ የተነደፉ ሁሉ ወደ ናሱ እባብ ሲመለከቱ ይድኑ ነበር። በእባብ የተነደፉ ሁሉ የናሱን እባብ ተመለክተዉ ይድኑ ዘንድ ይህ አስደሳች ዜና በመላዉ የእስራኤል ማሕበር ተሰራጨ። በንድፊያ ብዙዎች በማለቃቸዉና የተነደፉት ደግሞ የናሱን አይተዉ ይፈወሱ ዘንድ ሙሴ በእንጨት ላይ ሲሰቅለዉ አንዳንዶች አላመኑም ነበር። እነዚህ ካለማመናቸዉ የተነሳ ጠፉ። ብዙዎች ግን እግዚአብሔር ባዘጋጀዉ መፍትሔ እምነት ነበራቸዉ። . . . እነዚህ በንድፊያዉ የዛሉና ሊሞቱ የተቃረቡ ወገኖች እንደምንም ቀና ብለዉ ሲመለከቱ ፍጹም ይፈወሱ ነበር።

የፈዉስ ኃይል የሚወጣዉ ከእግዚአብሔር ብቻ እንደመሆኑ፤ ከናስ የተሠራዉ እባብ የተነደፈዉን ሰዉ ሊያድን የሚችል ኃይል እንደሌለዉ ሕዝቡ በሚገባ ያዉቅ ነበር። ጌታ በጥበቡ ኃይሉን በዚህ መልኩ መግለጥ መረጠ። በመረጠዉ በዚህ ቀላል መንገድ እስራኤላዊያን በኃጢአታቸዉ ምክንያት ይህ ሥቃይ እንደደረሰባቸዉ ተገነዘቡ። በተጨማሪ እግዚአብሔርን እስከታዘዙ ድረስ፤ እርሱ ጠባቂያቸዉ በመሆኑ፤ የሚፈሩበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር እንደማይገባ ማረጋገጫ ተሰጣቸዉ።”—አበዉና ነቢያት ገጽ 62፣ 63 (2)

ለ. ይህ ሁኔታ በቀደመዉ እባብ ንድፊያ ከሚሰቃዩት (ራእይ 12:9) እና ፈውስ ከሚሹት ጋር የሚመሳሰለዉ እንዴት ነው? ዮሐንስ 3:14፣ 15፤ 1፡29።

እርሱን በመመልከት ስለሚለወጥ ንስሃ የሚገባ ኃጢአተኛ ሁሉ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” የሆነዉን የሱስን ይመልከት። ዮሐ. 1፡29። ይህን ካደረገ ፍርሃቱ ወደ ደስታ፣ ጥርጣሬዉም ወደ ተስፋ ይለወጣል። አመስጋኝ ይሆናል። የድንጋይ ልቡ ይሰበራል። የፍቅር ማዕበል ነፍሱን ያጥለቀልቀዋል። ክርስቶስ በዉስጡ ሆና ለዘለዓለም ሕይወት የዉሃ ምንጭ ይሆንለታል።”— የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 453


ረቡዕ ጥር 10

4. የሱስ ማን ነው?

ሀ. ክርስቶስ በምድር ላይ ፍጹም ሕይወት ኖሯል (1ኛ ጴጥሮስ 2:21፣ 22) ሆኖም ወደ እሱና ወደ ታማኝ ተከታዮቹ ከመቅረብ ይልቅ የብዙ ሰዎች ምላሽ ምንድን ነው? 2ኛ ጢሞ 3:12፤ ዮሐንስ 3:19፣ 20

የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በርግጥም የተለዩ ሕዝቦች ነበሩ። ነቀፋ የሌለው ባህርያቸውና የማይዋዥቀው እምነታቸው የኃጢአተኛውን ሰላም የሚረብሽ ቀጣይ ተግሳጽ ነበር። በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም፣ ድሃዎች፣ ደረጃ-የለሽና የክብር ማዕረግ የሌላቸው የነበሩ ቢሆኑም ባህርያቸውና አስተምህሮዎቻቸው በታወቀበት ሥፍራ ሁሉ ለክፉ አድራጊዎች ድንጋጤ ነበሩ። ስለዚህ አቤል የእግዚአብሔር መሰልነት በሌለው ቃየን ይጠላ እንደነበር እነርሱም በኃጢአተኞች ተጠሉ። ቃየን አቤልን ለገደለበት ተመሳሳይ ምክንያት፣ የመንፈስ ቅዱስን ገደብ አሽቀንጥረው መጣል የሚፈልጉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ገደሉ። የዚህ ባህርይ ንጽህናና ቅድስና ለራስ ወዳድነታቸውና ለብልሹነታቸው የማያቋርጥ ነቀፋ ስለሆነባቸው፣ አይሁዳውያን የሱስን ያልተቀበሉትና የሰቀሉት በዚሁ ተመሳሳይ ምክንያት ነበር። ከክርስቶስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፣ ታማኝ ደቀ መዛሙርቱ የኃጢአትን መንገድ የሚወዱትንና የሚከተሉትን ጥላቻና ተቃውሞ ቀስቅሰዋል።”—The Great Controversy, p. 46.

ለ. የሰውን ልጅ የመሳብ አቅም ያለው በአለም አዳኝ ውስጥ የተገለጠው ከፍተኛ ሀይል የትኛው ነው? 1ኛ ጢሞቴዎስ 3:16፤ ዮሐንስ 1:1-3ዕብራውያን 1፡8

ክርስቶስ ሁሉን ከፈጠረ፣ እርሱ ከሁሉም በፊት ነበር። ይህንን በተመለከተ የተነገሩት ቃላት በጣም ወሳኝ ከመሆናቸው የተነሳ ማንም በጥርጣሬ ውስጥ ሊያስገባ አያስፈልግም። ክርስቶስ በመሠረቱ ፍጹም አምላክ ነበር። እርሱ ከዘላለም ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ፣ ለዘላለም የተባረከም ነው።”—Selected Messages, bk. 1, p. 247.

እግዚአብሔር በልጁ ላይ የደረሰዉን የመጨረሻ ሰበአዊ ስቃይ በጥቅጥቅ ጨለማ ከለለዉ። ክርስቶስ ሲሰቃይ ያዩት ሁሉ መለኮታዊነቱን አዉቀዋል። ያ ሰበአዊ ፍጡራን ያዩት ፊቱ ፈጽሞ የሚረሳ አልነበረም። የቃየል ፊት ነፍስ ገዳይነቱን እንዳሳወቀበት ሁሉ እንዲሁም በክርስቶስ ፊት ላይ የእግዚአብሔር ገጸ ባሕርይ የሆነዉ ንጽሕና፣ ፍጹም ሰላማዊነትና ርህሩህነት ይታይበት ነበር። የየሱስ ከሳሾች ግን ለሰማይ ማሕተም ደንታ አልነበራቸዉም። የሱስ የሚያፌዙበት ሰዎች ቀና ብለዉ እየተመለከቱት ለረጅም ሰዓታት ሲሰቃይ ቆየ፣ በኋላ ግን እግዚአብሔር በምህረቱ በካባዉ ከለለዉ።”— የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 799

የክርስቶስን ውርደት አስብ። የወደቀዉን፣ በኃጢአት የተዋረደዉንና የረከሰውን የሰዉን ልጅ ተፈጥሮ ለራሱ ወሰደ። በደላችንን ተሸክሞ ሀዘናችንንና ሀፍረታችንን ተቀበለ። ሰው የተከበበባቸውን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሟል። የሰውን ልጅ ከመለኮት ጋር አንድ አደረገ፤ መለኮታዊ መንፈስ በሥጋ ቤተ መቅደስ ውስጥም አደረ።”—The SDA Bible Com-mentary [E. G. White Comments], vol. 4, p. 1147


ሐሙስ ጥር 11

5. እግዚአብሔር ሥጋ ሆነ

ሀ. የሰውን ልጅ ከአስጨናቂው ሰቆቃና ተስፋ ቢስ ሁኔታ ለማዳን ይህ መለኮታዊ አካል ምን ሆነ? ዮሐንስ 1:14ዕብራውያን 2፡9

ለ. የሱስ ነውር በሌለው መለኮታዊ ማንነቱ ላይ ምን እንደወሰደ ግለጽ። ዕብራውያን 2:10፣11፣14፣17

ሐ. የሱስ በቀራኒዮ መስቀል ላይ የሚስበዉ ኃይል እንዲሠራ ምን ያህል ራሱን ዝቅ ማድረግ ነበረበት? ዕብራውያን 2:14ፊልጵስዩስ 2:6–8፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:8

ከዚህ አንፃር ሰዎች አንድ ቅንጣት ያክል ክብር (ከፍ ከፍ ማለት) ሊኖራቸው ይችላልን? መከራና ውርደት የሞላበትን የክርስቶስን ሕይወት ዲካ እንከተላለን እያሉ፤ ፈተና፣ ኀፍረትና ውርደት እንደማይሸከሙ ሆነው በኩራት አንገታቸዉን ቀና ማድረግ ይችላሉን? ለክርስቶስ ተከታዮች እላለሁ፡ ወደ ቀራንዮ ተመልከቱ እና ራሳችሁን ከፍ ከፍ በሚታደርጉበት በራሳችሁ ሀሳብ እፍረት ይሰማችሁ።

የሰማዩ ልዑል የተዋረደበት ይህ ሁሉ ውርደት፤ ለበደለኛዉና ለተወገዘዉ ለሰው ልጆች ነው። የሰውን ልጅ ከሥነ ምግባሩ ርኩሰት ለማንሣት ከዚያ ሊደረስበት የሚቻል ዝቅተኛ ጥልቀት እስከማይገኝበት ድረስ በውርደት እጅግ በጣም ዝቅ አለ።—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 5, pp. 1127, 1128.

ሁሉን ለእርሱ ስናስረክብ የትኛዉን ነዉ ለራሳችን የምናስቀረዉ? የሱስ በኃጢአት የተበከለዉን ልብ በደሙ ሲያነጻ፣ ሲያጠራና ወደር በሌለዉ ፍቅሩ ሲያድን፣ ሰበአዊ ፍጡር ግን ሁለንተናዉን ለእርሱ ማስረከቡ አስቸጋሪ እንደሆነ አድርጎ ሲያስብ ይስተዋላል። ይህ ሲነገር ሲሰማም ሆነ ሲጽፈዉ ያሳፍረኛል!

እግዚአብሔር አስፈላጊያችን የሆነዉን ማንኛዉንም ነገር እንተዉ ዘንድ አይጠይቀንም። እርሱ የሚያደርገዉ ነገር ሁሉ ለልጆች ደህንነት የሚበጀዉን ነዉ። ክርስቶስን ያልመረጡት ነፍሳት ሁሉ ለራሳቸዉ ጥቅም ከሚሹት ነገር ሁሉ በእጅጉ የላቀዉን ሊሰጣቸዉ የሚችል መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል።”—ወደ ክርስቶስ የሚያመራ መንገድ፣ ገጽ. 43


አርብ ጥር 12

የግል የግምገማ ጥያቄዎች

1. የአብርሃም ልጆች ከነበሩት ከአይሁዳውያን ምን ትምህርት እናገኛለን?

2. የመጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ልንስት የምንችለው እንዴት ነው?

3. በምድረ በዳ ከነበሩት ገዳይ እባቦች ምን ትምህርት ማግኘት እችላለሁ?

4. ወደ ቀራኒዮ ሰው መሳብ የሚቻለው በምንድን ነው?

5. የሱስ ኃጢአተኛ የሆነውን ሰብዓዊ ተፈጥሮ የለበሰው ለምንድን ነው?

 <<    >>