እሁድ
ህዳር 15
1. ጠማማ “ማስተዋል”
ሀ. ከየትኛው ከባድ ክፋት መጠንቀቅ አለብን— ለምንስ? ያእቆብ 3:14፣ 15
“የጠላትን ሃሳብ ለመቀበል ልቡን የሚከፍት፣ ክፉ አስተሳሰብን የሚቀበልና ቅናትን የሚወድ፣ ይህን ክፉ አስተሳሰቡን አዘውትሮ በተሳሳተ መንገድ ይገነዘባል፣ ይህም ልዩ አርቆ አሳቢነት፣ አድልዎ፣ ወይም ጥፋተኝነትን ለመለየትና የሌሎችን መጥፎ ዓላማ ለመረዳት የሚያስችል ልዩ ማስተዋል ነዉ ይለዋል። አንድ ውድ ስጦታ ለእሱ እንደተሰጠውም አድርጎ ይቆጥረዋል፤ ተስማምቶ መኖር ከሚገባቸዉ ወንድሞቹም ይለያል፤ በፍርድ ወንበርም ላይ ወጥቶ እርሱ ራሱ ከፈተና ሁሉ የበላይ እንደሆነ አድርጎ ስሕተት የሠራ በመሰለዉ ሰው ላይ ልቡን ይዘጋል። ከእንደዚህ ዓይነት ሰዉ የሱስ ይለያል (ከእርሱ ጋር አይሆንም)፣ እናም በራሱ በገዛ ብርሃኑ ድንግዝግዝታ ውስጥ እንዲሄድ ይተወዋል።
“ይህ መንፈስ ኃጢአተኞችን በታማኝነት ለመገሰጽና ለእውነት ለመቆም የሚያስፈልግ ነገር እንደሆነ በመናገር ከእናንተ መካከል ማንም ቢሆን ይህን በማድረጉ ለእዉነት እንደቆመ በማሰብ ከቶ አይመካ። እንዲህ ዓይነቱ ጥበብ ብዙ አድናቂዎች አሉት፣ ነገር ግን በጣም አታላይና ጎጂ ነው፡፡ ይህም ከላይ የመጣ ሳይሆን የያልታደሰ ልብ ፍሬ ነው። የዚህ ነገር መሠረቱ ራሱ ሰይጣን ነው። ማንም ከሳሽ ራሱን አስተዋይ አድርጎ አይቁጠር፤ እንደዚያ ካደረገ ይህንን የሰይጣንን ባሕርይ የማይገባዉን የጽድቅን ልብስ ያለብሰዋልና። ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእነዚህ ከሚያረክሱት ነገሮች ሁሉ የነፍሳችሁን ቤተ መቅደስ ታነጹ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ መራራ ሥር ናቸውና።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, pp. 936, 937.
ሰኞ
ህዳር 16
2. መርዛማ ባህሪይ
ሀ. የማይቀረውን የቅናት እና የጠብ ውጤት ይግለጹ። ያእቆብ 3፡16
“በተቋም ውስጥ ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በወንድሞች ላይ ክፉ ቃላትን በመናገር ደግነት የጎደላቸው ሐሳቦችን የሚረጭ ሰው፣ የሰበአዊን ልብ መጥፎ ስሜት ቀስቅሶ ከእርሱ ጋር በሚገናኙ ሁሉ ላይ የሚሰራን የክፋት እርሾ ሊዘራ ይችላል። በዚህ መንገድ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ድልን ይቀዳጃል፣ የሥራው ውጤትም እርሱ ከአብ ጋር አንድ እንደሆነ ደቀ መዛሙርቱ አንድ እንዲሆኑ የተማፀነዉን የአዳኙን ጸሎት ከንቱ ማድረግ ነው።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 937.
ለ. በነፍሳችን ጠላት ከተቀሰቀሰው የሰው ልጅ ዝንባሌ በተቃራኒ ከሌሎች ጋር እንዴት ልንገናኝ ይገባል? ዮሐንስ 13፡34
“አቋማቸውን ወይም ስራቸውን ሳትረዳ ግን በመንገዶቻቸውና በአመለካከታቸው ላይ ትችት ትሰጣለህ፣ እንዲሁም በግለሰቦቹ ላይ ፍርድህን ትሰጣለህ። ነገሮችን በራስህ አመለካከት (ላንተ በሚታይህ በኩል ብቻ) ትመለከታለህ ከዚያም በሁሉም አቅጣጫ ጉዳዮችን በቅንነት ሳትመለከት እነርሱ የሚሄዱበትን አካሄድ ለመጠየቅ ወይም ለማውገዝ ዝግጁ ትሆናለህ። ስለሌሎች ወንድሞች ግዴታቸዉ (ስለስራቸዉ) ምንም የምታወቀዉ ነገር የለህም እንዲሁም ለድርጊታቸው ሀላፊነት ሊሰማህ አይገባም፣ ነገር ግን አንተ ግዴታህን ተወጣ፣ የቀረዉን ለጌታ አሳልፈህ ስጥ። መንፈስህን በትዕግስት ያዝ፣ ሰላምንና የአእምሮ መረጋጋትህን ጠብቅ፣ እንዲሁም አመስጋኝ ሁን። . . .
“በጣም ስሜታዊ ነህ፣ እንዲሁም አንተ ከምታስበዉ በተቃራኒ መንገድ ያለዉን ሀሳብ የሚደግፍ ቃል ከተነገረህ ትጎዳለህ። በዚህም እንደተከሰስክ ወይም እንደተወገዝህ ይሰማሃል፣ ስለዚህ ራስህን መከላከልና ህይወትህን ማዳን እንዳለብህ ይሰማሃል፤ በዚህም ራስህን ለማዳን በምታደርገዉ ጥረት በራስህ በርግጥም ነፍስህን ታጣለህ። ለራስህ ለመሞትና የመታገሥና የትዕግሥት መንፈስ ለማዳበር ሊትሰራዉ የሚገባ ሥራ ከፊትህ አለህ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 424.
“አንዳቸዉ አንዳቸዉን የሚተቹና የሚኮንኑ እነዚያ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እየጣሱ ነው፣ እርሱንም እያስቆጡ ናቸው። እግዚአብሔርንም ሆነ ባልንጀሮቻቸውን አይወዱም። ወንድሞችና እህቶች፣ ትችት፣ ጥርጣሬንና ቅሬታን እናስወግድ እንዲሁም ስሜቶቻችንን እንቆጣጠር። አንዳንዶቹ በጣም ስሜታዊ ከመሆናቸው የተነሳ ምክንያታዊ ሊሆኑ አይችሉም። የእግዚአብሄርን ህግ መጠበቅ ምን ማለት እንደሆነና ህግን እየጠበቅክ ወይም እየጣስክ ስለመሆንህ እርግጠኛ ለመሆን በጣም ንቁ ሁን። አምላክ እንድንጠነቀቅ የሚፈልገው ስለዚህ ጉዳይ ነው።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 937.
ማክሰኞ
ህዳር 17
3. ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎችን ማስተናገድ
ሀ. የአምላክን ሕግ ስለሚወዱ ሰዎች ምን ተጽፏል? መዝሙረ ዳዊት 119:165
“የተያዝኩበት ሁኔታ ትክክል አይደለም (የሚገባኝን ክብር አላገኘሁም)፣ ተበድያለሁ፣ አንድ ሰው ሊያስጨንቀኝ ወይም ሊጎዳኝ ይፈልጋል ከሚለው ሃሳብ ውጣ። በስህተት ዓይን እያየህ ነህና። እነዚህን የተዛቡ ነገሮችን እንድትመለከት የሚመራህ ሰይጣን ነዉ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 424.
“ዓለም ኃጢአትን ይወዳል፣ እናም ጽድቅን ይጠላል፣ እናም ይህ በየሱስ ላይ ያሳዩት ጥላቻ ምክንያት ነበር። ወደር የሌለውን ፍቅሩን እምቢ ያሉ ሁሉ ክርስትናን የሚረብሻቸዉ ሆኖ ያገኙታል። የክርስቶስ ብርሃን ኃጢአታቸውን የሚሸፍነውን ጨለማ ጠራርጎ ያጠፋዋል፣ እንዲሁም መታደስ እንደሚያስፈልጋቸዉ ይገለጣል። የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖ የሚቀበሉ ከራሳቸው ጋር ጦርነት ሲጀምሩ፣ ኃጢአትን የሙጥኝ ያሉ ግን ከእውነትና ከተወካዮቹ ጋር ይዋጋሉ።
“በዚህም ጠብ ይፈጠራል፣ እንዲሁም የክርስቶስ ተከታዮች ሕዝቡን የሚያስጨንቁ ተደርገው ይከሰሳሉ። ነገር ግን የአለምን ጠላትነት የሚያመጣባቸው ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ህብረት ነው። የክርስቶስን ነቀፋ ተሸክመዋል። እነርሱ የምድር መኳንንት የናቁትን መንገድ እየሄዱ ነው። በሐዘን ሳይሆን በደስታ፣ ስደትን ይጋፈጣሉ። እያንዳንዱ እሳታማ ፈተና የሚያጠራ የእግዚአብሔር ወኪል ነው። እያንዳንዱ ፈተና ከእርሱ ጋር ተባባሪዎች ሆነዉ ለሚሠሩት ሥራ ገጣሚ ያደርጋቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ግጭት ለጽድቅ በሚደረገው ታላቅ ጦርነት ውስጥ የራሱ ቦታ አለው፣ እንዲሁም ምንቀበላቸዉ እያንዳንዱ ፈተና የመጨረሻውን የድል ደስታን እጥፍ ድርብ እንዲሆን ያደርገዋል። ይህን ግምት ውስጥ ስለሚያዉቁ እምነታቸውንና ትዕግሥታቸውን የሚፈትን ፈተና ከመፍራትና ከመራቅ ይልቅ በደስታ ይቀበላሉ።”—The Desire of Ages, p. 306.
ለ. ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ አንድ ነገር ሲፈጸምብንም ስለ ምን ነገር እናስታውሳለን? ማቴዎስ 5:11፣ 12፣ 41፤ 1ኛ ጴጥሮስ 4:12-15
“መለኮታዊ የሆነዉ የቤተ ክርስቲያን ራስ፣ የድል አድራጊዎች ሁሉ ኃያላን የሆነው እርሱ ተከታዮቹን ወደ ህይወቱ፣ ድካሙ፣ ራስን መካድ፣ ተጋድሎውና መከራው፣ በንቀት፣ ተቀባይነት በማጣት፣ በመሳለቅ፣ በስድብ፣ በፌዝ፣ በውሸት፣ መካከል አልፎ በቀራንዮ መንገድ ወደ ስቅለቱ ቦታ እንደወጣና እንዳሸነፈ፣ እነርሱም በዚህ መንገድ እንድጓዙና ለአሸናፊው ወደሚሰጠዉ ሽልማትና ክብር ለመድረስ ይበረታቱ ዘንድ ወደ ሕይወቱ ያመላክታቸዋል። ድል የሚረጋገጠው ደግሞ በእምነትና በመታዘዝ ነው። የክርስቶስን ቃላት በግል ጉዳያችን ላይ እንተገብረው።”—The Review and Herald, July 24, 1888.
ረቡዕ
ህዳር 18
4. ጥበብ ከላይ
ሀ. የሰማዩ ጥበብ የመጀመሪያው ባሕርይ ምንድን ነው—ይህስ ለእኛ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ያዕቆብ 3:17 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ ማቴዎስ 5፡8
“ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚያረክስ ምንም ነገር አይገባም። እዚያ የሚኖሩ ሁሉ ልባቸው ንጹሕ ይሆናሉ። ስለ የሱስ በሚማር ሰው ውስጥ፣ ለግዴለሽነት ጠባይ፣ ጨዋነት ለጎደለው ንግግርና ጨዋነት ለጎደለው አስተሳሰብ ያለው ጥላቻ እየጨመረ ይሄዳል። ክርስቶስ በልቡ ሲኖር፣ ሁል ጊዜ የአስተሳሰብና የባሕርይ ንፅህናና ማሻሻያ ይኖራል።
“ነገር ግን ‘ልበ ንጹሐን የሆኑ ብፁዓን ናቸው’ የሚለው የየሱስ ቃላት ጥልቅ ትርጉም አላቸው—ዓለም ንጽሕናን በሚረዳበት መንገድ ንጹሕ ማለት ብቻ ሳይሆን ሥጋዊ ከሆነ ነገር የራቀ፣ ከሥጋ ምኞትም የጸዳ እንዲሁም የነፍሱ ዓላማዎችና ዝንባሌዎች፣ ከኩራትና ከራስ ብቁነት የጸዳ፣ ትሑት፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ፣ እንደ ሕጻን ልጅ የሆነ የሚል ትርጉም ያላቸዉ ናቸዉ።”— Thoughts From the Mount of Bless¬ing, pp. 24, 25.
ለ. ለክርስቶስ ስንዘጋጅ ትኩረታችን ምን መሆን እንዳለበት አስረዳ። 1ኛ ዮሐንስ 3:2፣ 3
“በእለት ተእለት ልምዳችን [የእግዚአብሔርን] ቸርነትና ርህራሄን በሚያደርግልን እንክብካቤ እናስተውላለን። በልጁ ባህሪይ እናውቀዋለን። መንፈስ ቅዱስ ስለ እግዚአብ ሔርና ስለ እርሱ የላከውን እውነትን ወስዶ ለማስተዋልና ለልብ ይከፍታል። ልበ ንጹሐን እግዚአብሔርን እንደ አዳኛቸው በአዲስና በሚያምር ግንኙነት ያዩታል፤ እንዲሁም የባህሪውን ንጽህናና ፍቅር ሲያውቁ፣ የእርሱን መልክ ለማንፀባረቅ ይናፍቃሉ። እርሱን ንስሐ የገባ ልጁን ለማቀፍ እንደሚናፍቅ፣ አባት ያዩታል እናም ልባቸውም በማይነገር ደስታና በክብር ተሞልቷል።
“ልበ ንጹሕ የሆኑ ፈጣሪን በኃይሉ የእጁ ሥራ፣ በዓለማት ዉስጥ ባለ ውበት ይገነዘባሉ። በጽሑፍ በቃሉ ውስጥ የምሕረቱን፣ የቸርነቱንና የጸጋውን መገለጥ ይበልጥ ግልጽ በሆነ መስመር ያነባሉ። ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች የተሰወረው እውነት ለሕፃናት ይገለጣል። በዓለማዊ ጥበበኞች የማይታወቁ የእውነት ውበትና ክቡርነት፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅና ለመፈጸም ለሚታመኑ፣ እንደ ሕፃን ያለ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች በየጊዜው ይገለጣል። እኛ እራሳችን የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋዮች በመሆን እውነትን እንገነዘባለን።
“ልበ ንጹሕ የሆኑ በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዓለም ውስጥ በከፋፈለላቸው ጊዜ ዉስጥ ልክ እንደ እግዚአብሔር መገኘት ሆነዉ ይኖራሉ።”—Ibid., pp. 26, 27
ሐሙስ
ህዳር 19
5. ተጨማሪ አስፈላጊ ባህሪያት
ሀ. ከንጽህና ቀጥሎ፣ ያለእነሱ ተጽእኖዋችን ዋጋ የሚያጣባቸዉ አምስት የሰማይ ጥበብ ባህሪያትን ጥቀስ። ያዕቆብ 3፡17 (መካከለኛው ክፍል)።
“የክርስቶስ ደግነት፣ ጨዋነት፣ የዋህነትና ትሕትና ያስፈልጋችኋል። ለእግዚአብሔር ከተቀደስህ ለከፍተኛ አገልግሎት ሊዉሉ የሚችሉ ብዙ ጠቃሚ ብቃቶች አሉህ። በጭካኔና በሸካራነት ሳይሆን በደግነትና በአክብሮት ወደ ወንድሞችህ የመቅረብ አስፈላጊነት ሊሰማህ ይገባል። በእነሱ ላይ የበላይነትህን ለማስጠበቅ ብለህ በሚታሳየዉ ስል መንፈስ የምታደርስባቸዉን ጉዳት መጠኑን አታስተውልምና። በዩኒየናችሁ ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ክብርን፣ ደግነትን፣ መተማመንንና ፍቅርን ብትሰጣቸው ኖሮ ለማገልገል ድፍረትን በማጣት ተስፋ አይቆርጡም ነበር። በአድራጎትህ የወንድሞችህን ልብ ከአንተ ለይተሃል፤ ምክርህ በእነሱ ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው አድርገሃል።”—Christian Leadership, pp. 6, 7.
“የምትጠብቀው ነገር ካልተሳካ፣ ተስፋ መቁረጥና እረፍት ማጣት እንዲሁም ለውጥን በመመኘት አደጋ ላይ ትወድቃለህ። ለማንቋሸሽ፣ ለማዋረድ ዝንባሌን ማስወገድ አለቦት። የመውገዝ መንፈስ እንዲቀሰቀስ ከሚያደርግ ነገር ሁሉ ራቅ። ይህ መንፈስ በማንኛውም የረጅም ጊዜ ልምድ ባካበቱ አገልጋዮቹ ውስጥ መገኘቱ እግዚአብሔርን አያስደስተውም። ወጣቶች በትህትናና በቅንነት ከሆነ ዉስጣዊ ፍላጎትንና ቅንዓትን መግለጥ ተገቢ ነው። ነገር ግን የችኮላ ቅንዓትና የውግዘት መንፈስ ገና የጥቂት ዓመታት ልምድ ባላቸዉ ወጣቶች ላይ ሲገለጥ በጣም ጥሩ ያልሆነና አጸያፊ ነው። እንደዚህ ያለ ወዲያውኑ የወጣቱን ተጽዕኖ ሊያጠፋ የምችል ምንም ነገር የለም፡፡ የዋህነት፣ ርህራሄ፣ ትዕግስት፣ መቻል፣ በቀላሉ አለመበሳጨት፣ ሁሉንም መሸከም፣ ሁሉን ተስፋ ማድረግ፣ ሁሉንም ነገር መታገስ - እነዚህ ሰማያዊ በሆነው የፍቅር ዛፍ ላይ የሚያፈሩ ፍሬዎች ናቸው። ይህንን ዛፍ፣ ከተንከባከብን፣ ዘዉትር የማይጠወልግ አረንጓዴ ዛፍ ይሆናል፡፡ ቅርንጫፎቹ አይደርቁም፣ ቅጠሎቹም አይረግፉም፡፡ ያለማቋረጥ በሰማይ ጠል ስለሚጠጣ፣ የማይሞት፣ ዘላለማዊ ይሆናል።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 134, 135.
አርብ
ህዳር 20
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ነዉ፣ መሻታቸዉን መጠራጠርና ብልሃት ነዉ ብዬ ለመጥራት የሚፈተነዉ?
2. ሌሎችን የመተቸት ልማድ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጥሰው እንዴት ነው?
3. ሰዉ መርዛማ የሆነ ባህሪይ በእኔ ላይ ሲያሳይ ምን ማስታወስ አለብኝ?
4. “በንጹሕ ልብ” መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
5. በቀላሉ የሚቀረብና 'ለመጠይቅ' ይበልጥ ቀለል ያልኩ ሰዉ መሆን የምችለው እንዴት ነው?