Back to top

Sabbath Bible Lessons

ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ

 <<    >> 
7ኛ ትምህርት ሰንበት፣ ህዳር 07፣ 2017

አፋችንን ከመክፈት በፊት መጸለይ

የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፤ የተሳሳትሁትንም ንገሩኝ።” (ኢዮብ 6፡24)።

“በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ፍጹም ሰው ነው ሥጋንም ሁሉ ደግሞ ሊገታ ይችላል። በመንገዳችን ላይ የሚያበራው ብርሃን፣ ለህሊናችን የምናገረዉ እውነት ራሱ ነፍሳችንን ያወግዛትና ያጠፋታል፣ ወይም ይቀድሳትና ይለውጣታል። የምንኖረው በአማክሮ ጊዜ መገባደጃ ላይ ሲሆን በአጉል የታይታ ሥራ ለመርካት ተገቢ አይደለም።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 308.

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 50–55, 314–318; vol. 5, pp. 55–59, 175–177. 

እሁድ ህዳር 01

1. የእኛን የበላይ የመሆንን ጉጉት ማረጋጋት

ሀ. ሁልጊዜ ሌሎችን ለመቆጣጠር የሚጣደፉ ሰዎች ምን ማስታወስ አለባቸው? ያዕቆብ 3:1ማርቆስ 9፡35።

“አምላክ በነፍሳችን ላይ ለምኖረው ተጽዕኖ፣ በራሳችንም ሆነ በሌሎች ሰዎች ጉዳዮች ላይ ለሚደርሰው ተጽዕኖ እያንዳንዱን ሰው ተጠያቂ ያደርጋል።”—Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 102.

“በተፈጥሮ የሰው ልጅ በራሱ ላይ ያተኮረ አመለካከት ያለው ነው። ክርስቶስ ሊያስተምራቸው የሚፈልገውን ትምህርት ከሚማሩ ሰዎች ሕይወት ግን ራስ ወዳድነት ይጠፋል። የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች ይሆናሉ፣ ክርስቶስም በእነርሱ ይኖራል። ሁሉንም ሰዎች ተመሳሳይ ምኞት፣ ችሎታዎች፣ ፈተናዎችና ችግሮች፣ ርህራሄንና እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ እንደ ወንድማማቾች አድርገዉ ይመለከቷቸዋል።

“ባልንጀራን በፍፁምአናዋርድ። ስሕተቶችን ስናይ የራሳችንን ልምድ በመንገር የተሳሳቱትን ለመርዳት የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን - ከባድ ስህተቶችን በሠራን ጊዜ በሥራ ባልደረቦቻችን የተደረገልንን፣ ትዕግስትና ህብረት፣ ደግነትና እርዳታ፣ እንዴት ድፍረትና ተስፋ እንደሰጡን ልናካፍላቸዉ ይገባል።”—The Signs of the Times, May 11, 1904.


ሰኞ ህዳር 02

2. የተሻለ አመለካከትን ማዳበር

ሀ. የራሳቸውን ስህተት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ በሌሎች ላይ ጨካኝ ለሆኑ ሰዎች ምን ዓይነት ስለታም ተግሣጽ ተሰጥቷቸዋል? መክብብ 7:20ያዕቆብ 3፡2 (የመጀመሪያው ክፍል)።

“የራሳችሁን ጉድለት ለይታችሁ የጽድቅን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ አይገባችሁምን? እግዚአብሄር እንዳይዋረድ እና እውነት በስህተት እንዳይገለጽ እናንተ በሌሎች መንፈስ ላይ እንደምትሆኑ በራሳችሁ መንፈስ፣ ስሜትና ቃላቶች ላይ ንቁ ተቺ አትሁኑምን? ይህን ብታደርጉ ማስተዋላችሁ በእጅጉ ይሻሻላል። እውነት፣ ሕያው ቃል፣ ግልጽ በሆነ፣ በማያሻማ ልዩነት፣ በአጥንታችሁ ውስጥ እንደተዳፈነ እሳት ረመጥ እያቃጠለ ክርስቶስን ለዓለም በመወክል ይታያል። . . .

“ራሳቸውን መርማሪ ካደረጉት መካከል አንዳቸውም የቁጥጥር ሥልጣንን የወሰዱበትን ቦታ ዝንባሌ ማየት አልቻሉም? የጠራ መንፈሳዊ እይታቸው የት ነበር? በገዛ ዓይናቸው ውስጥ ምሰሶ ሳለ በወንድም ዓይን ያለውን ጉድፍ ለምን ማስተዋል ቻሉ?”— Testimonies to Ministers, pp. 295, 296.

ለ. አንድ ሰው የሞራል ፍጽምና ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳየው ምንድን ነው - እና ይህ እንዴት ብቻ ሊሆን ይችላል? ያእቆብ 3:2፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡5 (ሁለተኛ አጋማሽ)።

“የማይታዘዝ ምላስ ርኩስ ሥራውን ለመሥራት ሥፍራ በሚያገኝበት ቦታ የጌታ ደስታ ጸንቶ ሊቆይ አይችልም።

“በወንድሞቻቸው ላይ ክፉ የሚያስቡና የሚናገሩ ተጠራጣሪዎች የዲያብሎስን በትር ይዘዉ እየሰሩ መሆናቸውን ያስታውሱ። እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል በትጋትና በጸሎት እርዳታ የዚያ የታመመውን አባል፣ አንደበትን ለመፈወስ ይሥራ። እያንዳንዱ ሰው ጥቃቅን ልዩነቶችንና ስህተቶችን ያለ ተቋዋሞ ማሳለፍ የእርሱ ግዴታና ልዩ መብት እንደሆነ ይሰማው፡፡ አንድ ሰው የሠራውን ጥቃቅን ስሕተቶችን አታጉላ ፣ ነገር ግን በእርሱ ያለውን መልካም ነገር አስብ። እነዚህ ስህተቶች በሚታሰቡበትና በተነገሩ ቁጥር እየጨመሩ ይሄዳሉ። ተራራ የሚሆነው ከትንሽ ኮረብታ ነው። መጥፎ ስሜትና አለመተማመን ውጤቱ ነው።”—Australasian Union Conference Record, April 15, 1903.

“ቃልህን እንድትጠብቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ግባ። “በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ፍጹም ሰው ነው ሥጋንም ሁሉ ደግሞ ሊገታ ይችላል።" ያእቆብ 3፡2 ያስታውሱ የበቀል ንግግር አንድ ሰው ድል እንዳገኘ እንዲሰማው በጭራሽ አያደርገውም። ክርስቶስ የእናንተ ፋንታ ይናገር። ክፋትን ባለማሰብ የሚገኘውን በረከት እንዳታጣ።”—Testimonies for the Church, vol. 7, p. 243.


ማክሰኞ ህዳር 03

3. የሚጀምረው ከሥሩ ነው።

ሀ. ቂም ስንይዝ የሚከተለውን የተሳሳተ አቅጣጫ ይከታተሉ እና ይህንን ለማስወገድ ብቸኛውን መንገድ ያብራሩ። ዕብራውያን 12:15፤ ያእቆብ 3:3-5

“በባልሽና በበደሉሽ ሰዎች ላይ ቂምሽን ተንከባክበሽ፣ ነገር ግን የተሳሳትሽበትን ነገር ሳታስተውይ በራስሽ የተሳሳተ አካሄድ ጉዳዩን አባብሰሻል። ግፍ በፈጸሙብህ ሰዎች ላይ መንፈስህ መራራ ሆኖ፤ ስሜትህም ስድብና ዘለፋን እንድታወጣ አድርጎሃል። ይህ ሸክሙ ለከበደዉ ልብህ ጊዜያዊ እፎይታ ይሰጣል፣ ነገር ግን በነፍስህ ላይ ዘላቂ ጠባሳ ትቶልህ ያልፋል። ምላስ ትንሽ ብልት ነው፣ ነገር ግን አንተ የሚያቃጥል እሳት እስኪሆን ድረስ አላግባብ መጠቀምን አዳብረሃል፡፡

“እነዚህ ሁሉ ነገሮች መንፈሳዊ እድገትህን የሚፈትሹ ሆነዋል። እግዚአብሔር ግን ታጋሽና ይቅር ባይ መሆን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያያልና እንዴት እንደሚራራና እንደሚረዳ ያውቃል። ህይወትህን እንድታስተካክል፣ ጉድለቶችህን እንድታስተካክል ይፈልግብሃል። ጽኑና የማይታክት መንፈስህ በጸጋው እንዲገዛ ይፈልጋል። ከሁከትና ከክርክር ይልቅ ሰላምና ጸጥታ ያስፈልጋሃልና የእግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ አለብህ። የክርስቶስ ሃይማኖት ከስሜታዊነት መንቀሳቀስን እንድትቀንስና የበለጠ በተቀደሰ ምክንያታዊነትና ከተረጋጋ ፍርድ እንድትንቀሳቀስ ያዛል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 139.

ለ. ስለምንናገረው ቃል ምን ማስተዋል አለብን? ያእቆብ 3፡6

“ቃሎችህ ይናገራሉ፣ ሥራህም መዝገብህ ያለበትን ያሳያል።”—Ibid., vol. 1, pp. 698, 699

“እህት ኤፍ በስሜታዊነት ተነስታ ትንቀሳቀሳለች፣ እናም ስህተት ታገኛለች፣ በዚህም በወንድሞቿና እህቶቿ ላይ ብዙ ነገር ትናገራለች። ይህ ደግሞ በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ግራ መጋባትን ይፈጥራል።”—Ibid., vol. 2, p. 51.

በክርስቶስ አገልጋዮች ላይ የስድብና የሐሰት ቃላትን መፈለግ የሚወዱ እግዚአብሔር የሥራቸው ምስክር መሆኑን ያስታውሱ። የእነርሱ የስም ማጥፋት ንክኪ ነፍስ የሌላቸውን ግዑዝ ዕቃዎችን የሚያረክስ ሳይሆን ክርስቶስ በደሙ የገዛቸውን ሰዎች ባሕርይ የሚያረክስ ነውና። በብልጣሶር ቤተ መንግሥት ውስጥ በግድግዳዉ ላይ ቃላቶቹን የጻፈዉ እጅ በአምላክ ሕዝቦች ላይ የተፈጸመውን ማንኛውንም ኢፍትሐዊ ድርጊት ወይም ጭቆና በታማኝነት መዝግቧል።”—Ibid., vol. 5, pp. 244, 245


ረቡዕ ህዳር 04

4. እውነት ቢሆንም እንኳን . . .

ሀ. በዘመናችን በአደገኛ ሁኔታ የተለመደ ዝንባሌን በተመለከተ ምን ጠንካራ ተማጽኖ ቀርቧል? መዝሙረ ዳዊት 15:1-3፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡6

“በክፋት ደስ የሚሰኝ አንደበት፣ ሪፖርት አድርጉ፣ እኔም እከሰዋለሁ የሚለው ምላስ፣ በሐዋርያው ያዕቆብ መልዕክት በገሃነም እሳት እንደሚቃጠል ተነግሯል። በእያንዳንዱ በኩል እሳትን ይተፋልና፡፡ የንጹሃንን ስም የሚያጠፋው ወሬ ሻጭ ምን ግድ አለው? በሸክማቸው ስር እየሰመጡ ያሉትን ተስፋና ድፍረት ቢያጠፋም ከክፉ ስራው አይታቀብም። እሱ የሚታትረዉ ቅሌት-አፍቃሪ ወይም ሀሜት ወዳድ ዝንባሌውን ለማስደሰት ብቻ ነው። ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎችም ቢሆኑ ንጹሕ፣ ሐቀኛ፣ ክቡር እና ተወዳጅ የሆኑትን ሁሉ ዓይኖቻቸውን ጨፍነው የሚቃወሙትንና የማይስማሙበትን ነገሮች ብቻ ቆጥበው ለዓለም አሳትመውታል።

“ሰይጣን እንዲገባ እናንተ ራሳችሁ በሮችን ከፍታችኋል። በምርመራችሁ ወይም በስብሰባችሁ ላይ የተከበረ ቦታ ሰጥታችሁታል። ነገር ግን በታማኝነት ለዓመታት ለገነባዉ ለባህርይዉ ልቀት ክብር አላሳያችሁም። ቀናተኛ፣ የበቀል ምላሶች ከራሳቸው ሃሳብ ጋር የሚስማማ ቀለም ያላቸው ድርጊቶችና ምክንያቶች አሏችሁና። ጥቁር ነጭ፣ ነጭ ጥቁር ሆኖ እንዲታይ አድርጋችዋል። አንዳንዶች በንግግራችሁ እንደገና ሲቃወሟችሁ የምንናገረዉ 'እውነት ነው' ትላላችሁ። የተናገራችሁ ነገር እውነት መሆኑን አምናችሁ መቀበላችሁ ብቻ አካሄዳችሁን ትክክል የሚያደርግ ይመስላችኋልን? አይ፣ አይሆንም። እግዚአብሔር በእውነት በአንተ ላይ ሊነሱ የሚችሉትን ውንጀላዎች ሁሉ ወስዶ አንተን ለቅጣት ጅራፍ አሳልፎ ቢሰጥህ ቁስልህ በወንድም ----- ላይ ካደረስከው የበለጠና ጥልቅ ይሆን ነበር። ምንም እንኳን እውነታዎች ቢሆኑም የተሳሳተ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ጥቅም ላይ ሊዉሉ ይችላሉ። በእሱ ላይ ማንኛውንም ዘገባ ለመሰብሰብና ስሙን ለማበላሸትና ተጽዕኖዉን ለማጥፋት ልትጠቀምበት መብት የለህም። ለወንድምህ ያሳየሄዉን መንፈስ ጌታ ለአንተ ቢያሳይ ያለ ርኅራኄ ትጠፋለህ። ሕሊና የለህምን? እንደዚያ ሳይሆን አይቀርምና ፈራሁ። ይህ ሰይጣናዊ ድግምት ኃይሉን የሚያጣበት ጊዜ ገና አልደረሰም። ወንድም ---- እንደዚያ እንዳልሆነ አዉቃለሁ፣ ግን አንተ እንዳልከዉ ሁሉ ቢሆንም እንኳ አካሄድህ አሁንም ፍትሃዊ አይሆንም ነበር።

“በወንድማችን ላይ የሚሰነዘረውን ነቀፋ ስንሰማ ያንን ነቀፋ እንቀበላለን። . . . (መዝሙር 15:1–3]”— Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 57, 58.

ለ. በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ተብለው ከተጠቀሱት ሰባት ኃጢአቶች፣ ከአንደበታችን ጋር የተያያዙ ስንቶቹ ናቸው? ምሳሌ 6፡16-19


ሐሙስ ህዳር 05

5. የሚያቆስል መሳሪያ

ሀ. በጣም የተለመደውን የሃሜት ልማድ እንዴትና ለምን ማስወገድ አለብን? ኢዮብ 6:24ምሳሌ 11:13፤ 26፡20–22።

“እያንዳንዱ ሰው የሌሎችን ስህተት የሚነግሩት ሰዎች ጥፋቱን ምቹ አጋጣሚ ሲያገኙ በተመሣሣይ ሁኔታ ለሌላ ሰዉ እንደምናገሩ ቢያስታውስ ሃሜት ምንኛ ይንኮታኮት ነበር። ስለእነርሱ በሌላ መልክ ከማሰባችን በፊት ስለሁሉም ሰው በተለይም ስለወንድሞቻችንን በደንብ ለማሰብ መጣር አለብን። ክፉ ዘገባዎችን በችኮላ መከበል የለብንም። እነዚህ ብዙውን ጊዜ የምቀኝነት ወይም አለመግባባት ውጤቶች ናቸው፣ ወይም እነሱ ከማጋነን ወይም ከፊል እውነታዎችን በመግለጽ ሊሆኑ ይችላሉ። ምቀኝነት እና ጥርጣሬ አንድ ቦታ ከተፈቀደላቸው በኋላ እራሳቸውን እንደ እሾህ ያሰራጫሉ። አንድ ወንድም ቢሳሳት ለእሱ ያለህን መልካም ፍላጎትህ የምታሳይበት ጊዜ ነው። በደግነት ወደ እርሱ ሂዱ ፣ ክርስቶስ ለቤዛነቱ የከፈለውን ወሰን የለሽ ዋጋ በማስታወስ ከእርሱ ጋር ጸልዩ። በዚህ መንገድ ነፍስን ከሞት ማዳንና የኃጢያትን ከማባዛት ማቆም ትችላላችሁ።

“ጥቅሻ፣ ቃል፣ የድምፅ ቃና፣ ለመዋሸት በጣም አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላል፣ ልክ እንደ ጠንካራ ቀስት ወደ አንድ ልብ ውስጥ እየሰመጠ፣ የማይድን ቁስል ያመጣል። ስለዚህ እግዚአብሔር መልካም ሥራን በሚፈጽምበት ሰው ላይ ጥርጣሬ፣ ነቀፋ ሊወርድ ይችላል፣ እነዲሁም ተጽዕኖው ይጎዳል፣ ጥቅሙም ይጠፋል። ከአንዳንድ የእንስሳት ዝርያዎች ዉስጥ ከመካከላቸው አንዱ ቆስሎ ቢወድቅ ወዲያውኑ በባልንጀሮቹ ተዘልዝሎ ይዘነጠልና ይበላል። የክርስቲያን ስም በተሸከሙት ወንዶችና ሴቶችም ተመሳሳይ ጭካኔ የተሞላበት መንፈስ እየታየ ነው። ከራሳቸው ያነሰ ጥፋተኛ የሆኑትን ሌሎችን በድንጋይ ለመውገር የፈሪሳዩያንን ቅንዓት ያሳያሉ። የሌሎችን ስህተት የሚጠቁሙና ትኩረታቸውን ከራሳቸው ለማራቅ ወይም ለአምላክና ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ቅንዓት እንዳላቸው ለማስመሰል ይህን የሚያደርጉ አሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 58, 59.

“ከስራ ፈት፣ ከንቱና ተንኮለኛ ወሬዎችን ለማዳመጥ የሚዉለዉ ጊዜ በከንቱ ከባከነዉ ይልቅ በጣም የከፋ ነዉና፤ ከፍ ያሉና ላቅ ላሉት ነገሮች ለማሰላሰል መሰጠት አለበት።”—Ibid., p. 176.


አርብ ህዳር 06

የግል ግምገማ ጥያቄዎች

1. ስለ ሁሉም ነገር አስተያየት የመስጠት ዝንባሌን መቀነስ ማድረግ ያለብኝ ለምንድነዉ?

2. ብዙውን ጊዜ ችላ የሚባለዉን የክርስቶስን መሳይ ባሕርይ አንድ አስፈላጊ ገጽታ ጥቀስ።

3. የእምነት ባልንጀሮቻችንን በሌሎች ፊት ስናጎድፍ አምላክ እንዴት ይመለከተዋል?

4. ከመዝሙር ዳዊት ምዐራፍ 15 ምን መማር አለብኝ—ይህስ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?

5. በወንድማማቾች መካከል ጠብ በመዝራት ጥፋተኛ መሆን የምችለው እንዴት ነዉ እንዲሁመ፣ ማቆም ያለብኝ ለምንድነዉ?

 <<    >>