እሁድ
ጥቅምት 24
1. እምነት እና ምሳሌ
ሀ. ከምንናገረው እምነት ጋር ሙሉ በሙሉ ተስማምቶ መኖር በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 4:9፤ 1ኛ ዮሐንስ 5:3፤ ያእቆብ 2፡14
ሆን ብለው የአምላክን መሥፈርቶች እየጣሱ ቅዱሳን ሊሆኑ እንደሚችሉ በማመን ራሳቸውን አያታልሉ። እያወቁ ኃጢአት መሥራት የመንፈስን ምሥክርነት ድምፅ ጸጥ ያደርገዋል እንዲሁም ነፍስን ከእግዚአብሔር ይለያል።”—The Great Controversy, p. 472.
“የአንድ ሰው የሕይወት ምስክርነት ለሚመሰክረው እምነት ታማኝ መሆን አለመሆኑን ለዓለም ይናገራል። ምግባራችሁ በዓለማዊ ጓደኞችህ ግምት የእግዚአብሔርን ህግ ዋጋ ይቀንሳል። ለእነሱ እንዲህ የሚል መልዕክት ያስተላልፍላቸዋል:- 'ትእዛዛትን መታዘዝም ወይም አለመታዘዝም ይቻላል። የእግዚአብሔር ህግ በሰዎች ላይ አስገዳጅ የሚሆንበት ሁኔታ እንዳለ አምናለሁ፤ ነገር ግን፣ ከሁሉም በላይ፣ ጌታ ትእዛዛቱን በጥብቅ እንድንታዘዝ ቆራጥ ግዴታ አላስቀመጠም፣ ስለዚህ አልፎ አልፎ የሚፈጸም መተላለፍን እርሱ አክብዶ አይመለከተዉም።'
“ብዙዎች የአንተን ምሳሌ በመጥቀስ ሰንበትን ስለጣሱ ለራሳቸው ሰበብ ያቀርባሉ። ሰባተኛው ቀን ሰንበት ነው ብሎ የሚያምን መልካም ሰው ሁኔታዎቹ አስቸጋሪ በሚመስልበት ቀን ዓለማዊ ሥራ መሥራት ከቻለ፣ ሌሎቹም ያለምንም ኩነኔ ያንኑ ማድረግ እንደሚችሉ ይከራከራሉ። ብዙ ነፍሳት ለእግዚአብሔር ህግ አለመታዘዛቸው ምክንያት የአንተ ተጽእኖ ሰበብ እንደሆነ በመግለጽ ከአንተ ጋር በፍርድ ቀን ፊት ለፊት ይጋፈጣሉ። ምንም እንኳን ይህ ለኃጢአታቸው ይቅርታ ባያሰጥም በአንተ ላይ ግን በሚያስፈራ ሁኔታ ይነገራል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 250.
ሰኞ
ጥቅምት 25
2. ሰማይና ምድር እየተመለከቱ ነው
ሀ. ያዕቆብ ከድርጊት የለሌዉ ባዶ ንግግር ግብዝነት ለማሳየት ምን ምሳሌ ሰጥቷል? ያዕቆብ 2፡15-17
“በአሥርቱ ትእዛዛት ሕግ ላይ ሊሰበክ የሚችለው እጅግ አስደናቂ ስብከት እነርሱን በሕይወታችን በመታዘዝ ተግባራዊ ማድረግ ነዉ፡፡ ይህም የግል ግዴታ መሆን አለበት። የዚህ ግዴታ ቸልተኝነት ግልጽ ኃጢአት ነው። እግዚአብሔር ለራሳችን መንግሥተ ሰማያትን እንድናገኝ ብቻ ሳይሆን መንገዱን ለሌሎች ማሳየት እና በእኛ እንክብካቤ እና ራስ ወዳድነት በሌለዉ ፍቅራችን፣ በተጽእኖአችን ክልል ውስጥ የሚመጡትን ወደ ክርስቶስ መምራት አስገዳጅ ግዴታ እንደሆነ እንዲሰማን እግዚአብሄር በነዚህ ግዴታዎች ውስጥ ያስቀምጠናል። የብዙ ክርስቲያን ነን ባዮችን ሕይወት የሚያመለክት መርህ አለመኖሩ አሳሳቢ ነው። የአምላክን ሕግ ችላ ማለታቸው የተቀደሰ የይገባኛል ጥያቄዎቹን የሚገነዘቡትን ሰዎች ያሳዝናል፤ እንዲሁም ይህን ሕግ አዲስ የሚቀበሉትን ከእውነት እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 58. [Author’s emphasis.]
ለ. በክርስቶስ ላይ ያለ እውነተኛ እምነት ማለት ምን ማለት ነው? ያዕቆብ 2:18፤ ማቴዎስ 6፡24
“እግዚአብሔር ተናግሯል፣ እናም ይህ ማለት ደግሞ ሰው መታዘዝ አለበት ማለት ነው። ይህን ለማድረግ የሚመች እንደሆነ አይጠይቅም። የሕይወትና የክብር ጌታ ሰውን ካለመታዘዝ መዘዝ ለማዳን ውርደትንና ሞትን ተቀብሎ የሐዘን ሰው ሆኖ ከኃዘን ጋር የተዋወቀው የሥልጣን ቦታውን ለቆ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ምቾቱንና ተድላውን አልጠየቀምና። የሱስ የሞተው ሰውን በኃጢአቱ ለማዳን ሳይሆን ከኃጢአቱ ለማዳን ነው። ሰው የስህተት መንገዱን ትቶ የክርስቶስን አርአያ በመከተል መስቀሉን ተሸክሞ እርሱን በመከተል ራሱን በመካድ በምንም ዋጋ እግዚአብሔርን መታዘዝ አለበት። . . .
“እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች ከሆንን ትእዛዛቱን እንደምንታዘዝ ወይም የራሳችንን ጊዜያዊ ጥቅም እንደምናስከብር በአእምሮአችን ውስጥ ምንም ዓይነት ጥያቄ ሊኖር አይገባም። በዚህ በአንጻራዊነት ሰላማዊ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ በእውነት ውስጥ ያሉ አማኞች በእምነታቸው ካልጸኑ፣ ታላቁ ፈተና ሲመጣና የአውሬውን ምስል በማይሰግዱና ምልክቱን ግንባራቸዉ ወይም በእጃቸው በማይቀበሉ ሁሉ ላይ አዋጁ ሲወጣ ምን ይሆናሉ? ይህ ታላቅ ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ የአምላክ ሕዝቦች ደካማና ተስፋ ቢስ ከመሆን ይልቅ በችግር ጊዜ ብርታትንና ድፍረትን ማሰባሰብ ይኖርባቸዋል።”—Ibid., pp. 250, 251. [Author’s emphasis.]
ማክሰኞ
ጥቅምት 26
3. ከአብርሃም መማር
ሀ. በጥብቅ ማስጠንቀቂያ የተሰጠን ስለ የትኛው መንፈሳዊ ሁኔታ ነው? ያእቆብ 2፡19
የአለም አዳኝ እንደሆነ አምነዋል ፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ ራሳቸውን ከእርሱ ያርቃሉ፣ እናም ከኃጢአታቸው ንስሐ ስለማይገቡ፣ የሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው መቀበል ተስኗቸዋል። የእነሱ እምነት በቀላሉ የአዕምሮ ስምምነት እና ለእውነት መፍረድ ነው፤ እውነት ግን ነፍስን እንዲቀድስና ባሕርይን እንዲለውጥ ወደ ልብ ውስጥ አይገባም።”—Selected Messages, bk. 1, pp. 389, 390.
“እውነትን ሁሉ ታምኑ ይሆናል፤ ሆኖም የእሱ መርሆዎች በህይወታችሁ ውስጥ ተግባራዊ ካላደረጋችሁ እምነታችሁ አያድናችሁም፡፡ ሰይጣን አምኖ ይንቀጠቀጣል። ሥራዉንም ይሰራል። ዘመኑ አጭር እንደሆነ ያውቃል እናም እንደ እምነቱ ክፉ ስራውን ለመስራት በታላቅ ሀይል ወርዷል። የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን የሚሉ ሰዎች ግን እምነታቸውን በሥራ አይደግፉም። ጊዜዉ አጭር እንደሆነ ያምናሉ፣ ነገር ግን ዓለም አሁን ባለበት ሁኔታ ለሺህ ዓመትታ የሚቆይ ያህል የዚህን ዓለም መዝገብ ለማከማቸት በጉጉት ይሯሯጣሉ።”—Testimo¬nies for the Church, vol. 2, p. 161.
ለ. በአብርሃም ምሳሌ መነሳሳት የምንችለው እንዴት ነው? ሮሜ 4:1-3፤ ያዕቆብ 2፡20-22
“አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ። ማመኑን እንዴት እናውቃለን? ሥራውም የእምነቱን ባሕርይ ይመሰክራል፣ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።”
“በዘመናችንየእግዚአብሔርን ፍቅር ጣፋጭ ብርሃን ለመሸፈን እና መንፈሳዊ እድገትን ድንክዬ ለማድረግ በዙሪያችን የሚሰበሰበውን ጨለማ ለማብራት የአብርሃም እምነት ያስፈልገናል። . . . እያንዳንዱ የተከናወነው ተግባር፣ በየሱስ ስም የሚከፈል መስዋዕትነት ሁሉ እጅግ የላቀ ሽልማት ያስገኛል። ሰዉ ግዴታውን በሚወጣበት ጊዜ አምላክ ይናገራል እንዲሁም ይባርካል።”—The SDA Bible Com¬mentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 936.
“ሰዎች በእምነት ይጸድቃሉ፣ ነገር ግን የሚፈረድባቸውና የሚሸለሙት እንደ ሥራቸው ነው።”—The Signs of the Times, November 20, 1884.
“የክርስቶስ ጽድቅ በትክክለኛ ሥራ እና ከንጹሕ እንዲሁም ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ውስጣዊ ግፊት የሚገኝ መልካም ሥራዎችን ያካትታል።”—Testimonies for the Church, vol. 3, p. 528.
“የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ማክበር ከእኛ የሚፈልገው መልካም ስራን፣ ራስን መካድ፣ ራስን መስዋዕትነትን እና ለሌሎች መልካም ለማድረግ መስዋዕት መሆንን የሚጠይቅ ነው፤ መልካም ስራችን ብቻ ሊያድነን አይችልም ነገር ግን ያለ መልካም ስራ በእርግጠኝነት መዳን እንደማንችል ግልጽ ነው። ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ማለት ያለብን፡- “ግዴታችን ብቻ ነዉ የተወጣነዉ ፣ ከእግዚአብሄር ዘንድ ትንሽ ዉለታ እንኳን የማይገባን የማንጠቅም አገልጋዮች ነን” ነዉ። ክርስቶስ ጽድቃችንና የደስታችን አክሊል ሊሆን ይገባዋል።”—Ibid., p. 526.
ረቡዕ
ጥቅምት 27
4. የማበረታቻ ቃላት
ሀ. የአብርሃም ሕይወት ምሳሌ በእኛ በክርስቶስ አማኞች በራሳችን ሕይወት ውስጥ እንዴት መንጸባረቅ እንዳለበት አስረዳ። ዘፍጥረት 26:5፤ ያእቆብ 2:23፣ 24
“መልካም ሥራዎች የእምነት ፍሬዎች ናቸው። እግዚአብሔር በልቡ ሲሠራ፣ ሰውም ፈቃዱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ሲሰጥ፣ እና ከእግዚአብሔር ጋር ሲተባበር፣ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን በሕይወቱ ይሠራል፣ በልቡ ዓላማና በሕይወቱ ሥራ ልምምድ መካከልም ስምምነት ይኖራል። እያንዳንዱን ኃጢአት የሕይወትና የክብር ጌታን እንደ ሰቀለው ክፉ ነገር አድርገዉ መጸየፍ አለበት፣ እናም አማኙ የክርስቶስን ሥራዎች ያለማቋረጥ በመሥራት ተራማጅ ልምድ ሊኖረው ይገባል። ቀጣይነት ባለው የፈቃድ እጅ በመስጠት፣ በማያቋርጥ መታዘዝና፣ የፅድቅ በረከት የሚቆየው።
“በእምነት የሚጸድቁ የጌታን መንገድ የሚጠብቅ ልብ ሊኖራቸው ይገባል። ሰው ሥራው ከእምነቱ ጋር በማይጣጣምበት ጊዜ በእምነቱ እንደማይጸድቅ ማስረጃ ነው። ያዕቆብ ‘እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን? (ያእቆብ 2፡22)
“መልካም ሥራ የማያደርግ እምነት ነፍስን አያጸድቅም።”—Selected Messages, bk. 1, p. 397.
ለ. በዛሬው ጊዜ ለአረማውያን የሚመሰክሩ ሁሉ አምላክ ያጸደቃት ጋለሞታይቱ ረዓብ መጠቀሷ ሊያበረታታ የሚችለው እንዴት ነው? ያዕቆብ 2:25፤ ዕብራውያን 11፡31
“በክፉዋ ኢያሪኮ የአሕዛብ ሴት ምስክርነት፡- አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ ነው። ኢያሱ 2፡11 በዚህ መንገድ የመጣላት የአምላክ እውቀት መዳንዋን አረጋግጧል። . . . እሷም መመለሷ አምላክ መለኮታዊ ሥልጣኑን ለተቀበሉ ጣዖት አምላኪዎች የነበሩ ቢሆኑም እንኳን ያለውን ምሕረት የሚያሳይ ነበር።”—Prophets and Kings, p. 369.
ሞዓባዊቷ እንደ ሩት ከጣዖት አምልኮ ወደ እውነተኛው አምላክ አምልኮ የተመለሱ ሁሉ ከተመረጠው ሕዝብ ጋር ራሳቸውን አንድ ማድረግ ነበረባቸው።”—Christ’s Object Lessons, p. 290.
“ታላቅ ሥራ በከተሞቻችን ይሠራል፤ እርሻውም ሁሉ መከሩ ደርቋል። በክርስቲያንም ሆነ በአረማውያን አገሮች ያሉ ንስሐ የገቡ ነፍሳት ለእርዳታ ድምጻቸውን ያሰሙ ዘንድ ትኩረታችን በሁሉም አቅጣጫ ይጠራሉ። ራስን ከፍ ከፍ የምናደርግበት አንድት ቅንጣት ነገር እንኳ መኖር የለበትም፤ ደህንነታችን በአምላክ በመታመን ብቻ ነውና።”—The General Conference Bulletin, April 1, 1895.
ሐሙስ
ጥቅምት 28
5. የድል ቁልፎች
ሀ. በክርስቶስ ድል እንዴት እንደምንሆን አስረዳ። ያዕቆብ 2:26፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1:3፣ 4
“በየሱስ ማመን እና በእርሱ መዳናችሁን ማመን አስፈላጊ ነው። ዳሩ ግን ብዙዎች 'ድኛለሁ' ብለው የሚወስዱትን አቋም መያዝ አደጋ አለው። ብዙዎች:- “መልካም ሥራን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ” ይላሉ፤ ነገር ግን ከክርስቶስ በቀር ማንም መልካምን ማድረግ አይችልም። በአሁኑ ጊዜ ብዙዎች 'እመኑ፣ ብቻ እመኑና ኑሩ' ይላሉ። እምነት እና ስራ አብረው ይሄዳሉ፣ ማመን እና መስራት የተዋሃዱ ናቸው። ጌታ አሁን አዳም ከመውደቁ በፊት በገነት ውስጥ ከጠየቀው ያነሰ ነገር ከእኛ ነፍስ አይፈልግም - እሱም ፍጹም ታዛዥነትንና እንከን የለሽ ጽድቅ ነዉ። በጸጋው ቃል ኪዳን ስር ያለው የእግዚአብሔር መስፈርት ልክ በገነት ውስጥ እንዳደረገው መስፈርት ሰፊ ነው—ቅዱስ፣ ጻድቅ እና መልካም ከሆነው ከህጉ ጋር የሚስማማ። . . . ማንም ሰው፣ ምንም እምነት ቢኖረውም፣ ሕይወት የቱንም ያህል ፍጹም ባይሆንም እግዚአብሔር ቅንነትን ይቀበላል በሚል የተፈጥሮ ልብን ደስ በሚያሰኝ ማታለል አይወሰድ፡፡ እግዚአብሔር ከልጆቹ ፍጹም ታዛዥነትን ይፈልጋል።
“የሕግ መስፈርቶችን ለማሟላት በእምነት የክርስቶስን ጽድቅ እንደ ጽድቃችን መቀበል አለብን። ከክርስቶስ ጋር በመተባበር፣ በእምነት ጽድቁን በመቀበል፣ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት፣ ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች ለመሆን ብቁ እንሆናለን። ከክፉው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ለመንገድ ፍቃደኛ ከሆናችሁ እና ዘላለማዊ ጽድቅ እንዲመጣ ዘንድ ከሰማያዊ ወኪሎች ጋር በቤተሰብዎ እና በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለውን በደል ለመከልከል ካልተባበራችሁ፣ እምነት የላችሁም ማለት ነዉ። እምነት የሚሠራው በፍቅር ነው ነፍስንም ያነጻል። በእምነት መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ቅድስና ለመፍጠር በልብ ይሠራል፤ ነገር ግን ይህ የሰው ወኪል ከክርስቶስ ጋር ካልሰራ በስተቀር ማድረግ አይቻልም። . . . የክርስቶስ ጽድቅ እንዲኖረን በየዕለቱ በመንፈስ ተጽዕኖ መለወጥና የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድንሆን ያስፈልገናል።”—Selected Messages, bk. 1, pp. 373, 374.
አርብ
ጥቅምት 29
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. የአምላክን ሕግ እንደምጠብቅ ሰዉ ስለ ተጽዕኖዬ ምን መገንዘብ አለብኝ?
2. ሰማይ ከክርስቲያን አማኞች ምን ይፈልጋል?
3. አብርሃም ብዙ ጊዜ የአማኞች አባት ተብሎ የሚጠራው ለምንድን ነው?
4. ከማውቃቸው ሰዎች መካከል፣ የተለወጠችው ረዓብ ማን ሊሆን ይችላል?
5. የድል አድራጊ ክርስቲያናዊ ልምድን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?