እሁድ
ግንቦት 04
1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥራት ብዙ ጊዜ ችላ ይባላል
ሀ. በዛሬው ጊዜ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ውድቅ የሚያደርጉት ግን ለቤተሰብ ደስታ መሠረታዊ ሥርዓት የትኛው ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:1 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ ኤፌሶን 5:22-24፤ ቆላስይስ 3፡18
“እህቴ፣ ስታገቢ ከባልሽ ምን ጠበቅሽ ነበር? በገዛ እጅሽ ስልጣን ወስደሽ ፈቃዱን ከዛ ጠማማና ግትር ፍላጎትሽ ጋር ለማስማማት ጠብቀሽ ነበር? ባልሽ በትዳር ህይወቱ ምን ያህል እረፍት፣ እርካታ፣ ሰላም እና ደስታ አግኝቷልን? በጥቅቱ ብቻ። . . . ሚስት እራሷን እንደ አሻንጉሊት መቁጠር የለባትም፣ እውነተኛ ሴት ፣ በትከሻዋ በምናባዊ ሳይሆን ትክክለኛ ሸክም ተሸክማ በማስተዋል፣ በአሳቢነት የተሞላ ህይወት የምትኖር እንጂ፣ በምናባዊ ሸክም ራሷን የምታደክም መሆን የለባትም፤ ከእራሷ ውጭ ሌሎች ሊታስብባቸው የሚገቡ ነገሮች እንዳሉ በማሰብ ይኖርባታል።
“ባልሽ እግዚአብሔር ስለአንቺ ያሳየኝን ዓይነት ሆነሽ ሲያገኝሽ ቅር የሚሰኝ አይመስልሽም? ሸክም እንዳትሸከሚ፣ ምንም ዓይነት ግራ መጋባት እንዳይኖር፣ እራስሽን እንዳትክጅ ጠብቆ ያገባሽ ይመስልሻልን? ራስሽን የመግዛት፣ ደስተኛ፣ ደግ፣ ታጋሽና አስተዋይ የመሆን ግዴታ እንደሌለብሽ ይሰማሽ ይሆንን?”—Manuscript Releases, vol. 17, pp. 310, 311.
ለ. የተለወጠች ሚስት ያላመነ ባሏን ለመድረስ በጣም ውጤታማው መንገድ ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:1፣ 2፤ 1ኛ ቆረንቶስ 7:10፣ 13፣ 14።
ሰኞ
ግንቦት 05
2. ተስማሚ ግንኙነትን ማሳደግ
ሀ. ሚስት ከባልዋ ጋር ላለው ግንኙነት ጴጥሮስ ምን ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ይጠቀማል? 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4-6 በዚህ ግንኙነት ውስጥ የተገለጠውን ሚዛን ያብራሩ። ዘፍጥረት 21:9-12
“ስለ ጋብቻ ግንኙነት ቅዱስነት ለአብርሃም የተሰጠው መመሪያ ለሁሉም ዘመን የሚሆን ትምህርት ነበር። የዚህ ግንኙነት መብትና ደስታ በታላቅ መስዋዕትነትም ቢሆን በጥንቃቄ ሊጠበቅ እንደሚገባ ያውጃል። የአብርሃም እውነተኛ ሚስት ሣራ ብቻ ነበረች። እንደ ሚስትና እናት መብቷ ማንም ሌላ ሰው ሊጋራው አልቻለም። ባሏን ታከብራለች፣ እናም በዚህ ውስጥ በአዲስ ኪዳን እንደ ብቁ ምሳሌ ተቀምጣለች። እርስዋ ግን የአብርሃም ፍቅር ለሌላው እንዲሰጥ አልፈለገችም ነበር፤ አምላክም ተቀናቃኟ እንድትባረር በመፈለጓ አልገሰጻትም።”— Patriarchs and Prophets, p. 147.
ለ. አንድን ባል በቤተሰብ ክበብ ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚያሳዝነው እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ስም የሚያበላሽ ምንድን ነው? ምሳሌ 14:1፤ 25:24፤ 27:15፤ ይህንን ከ1ኛ ጴጥሮስ 3፡4 ጋር አወዳድር።
“በጣም ብዙ ባሎች እና ልጆች በቤት ውስጥ ምንም የሚማርክ ነገር የማያገኙ፣ ያለማቋረጥ የነቀፋና የማጉረምረም ሰላምታ የሚያገኙ፣ ከቤት ርቀው መፅናናትንና መዝናኛን ይፈልጋሉ። . . . ሚስት እና እናት በቤተሰቧ እንክብካቤ ስለምትወጠር፣ ምንም እንኳን በእነርሱ ፊት ልዩ የሆነ ብስጭትና ንዴት ባታሳይም፣ ቤቷን ለባሏና ለልጆቿ ሊያስደስታቸው የሚችሉ ጥቃቅን ነገሮችን ችላ ትላቸዋለች። እሷ የሚበላውን ወይም የሚለበሰውን ነገር በማዘጋጀት ተወጥራ ባሏና ልጆቿ እንግዳ ሆነው ገብተው ይወጣሉ።
“የቤተሰቡ እመቤት ተግባሯን በትክክል ብትፈጽምም፣ ፣ እና የእርሷን ሃላፊነትና ሰራዎችን በማጋነን እጣ ፈንታዋን ከሴቶች ከፍተኛ ህይወት ነዉ ብላ ከሚታስበዉ ሕይወት ጋር በማነፃፀር ነው የተጫነባትን ባርነት በመቃወም ያለማቋረጥ እየጮኸች ሊሆን ይችላል። . . . ምንም ፍሬ ቢስ በሆነ መልኩ የተለየ ሕይወት ለማግኘት ስትመኝ፣ የኃጢአት ብስጭት እየመገበችና ቤቷን ለባሏና ለልጆቿ በጣም ደስ የማይል እያደረገች ነው።”— The Adventist Home, p. 249.
“ለእግዚአብሔር ያላደረች የአገልጋይ ሚስት ለባሏ ምንም አትረዳም። መስቀልን መሸከም አስፈላጊ እንደሆነ በማሰብና ራስን የመካድ አስፈላጊነትን ሲያበረታታ የሚስቱ የዕለት ተዕለት ምሳሌ ከስብከቱ ጋር የሚጋጭ ከመሆኑም ሌላ ኃይሉን ያጠፋል።”— Gospel Workers, p. 210. [1892 edition.]
ማክሰኞ
ግንቦት 06
3. አደገኛ የኩራት ዓይነቶች
ሀ. አንዲት ክርስቲያን ሚስት ራሷን ማራኪ የምታደርገው እንዴት ነው? ምሳሌ 31:25-29
“[ሚስትቱ] ባሏን ከራሷ ጋር የበለጠ ማቆራኘት እንዲሁም በእርሱ ላይ በጥብቅ በመታመን ቤቷን አስደሳችና ማራኪ ለማድረግ የተቻላትን ሁሉ በትጋት ማድረግ አለባት።”— Testimonies for the Church, vol. 5, p. 598.
“በማንም ላይ የሚታይ ዝርክርክነት ቸልተኛነትና ጥንቁቅ አለመሆን ጌታን አያስደስተውም። እነዚህ ጉድለቶች ከባድ ጥፋቶች ናቸው። በሥርዓት የተቀጡ ልጆችንና ጥሩ ቁጥጥር ያለውን ቤት ለሚወድ ባል የእነዚህ ነገሮች መጓደል ለሚስቱ ያለውን ፍቅር እንዲቀንስ የሚያደርጉት ናቸው። አንዲት ሚስትና እናት ሥርዓትን የማትወድ ከሆነ፤ ክብሯን የማትጠብቅ ከሆነና፤ ጥሩ አስተዳደግ ከሌላት፤ ለቤተሰቧ መስማማትንና ደስታን ልታመጣ አትችልም። በነዚህም ነጥቦች ግድፈት ያለባቸው ሁሉ ወዲያውኑ እራሳቸውን ማስተማር መጀመር አለባቸው። ጉድለታቸው ብሶ በሚታይበት ጎን የበለጠ በመሥራት ለማሻሻል መጣር ይኖርባቸዋል።”— The Adventist Home, pp. 22, 23.
ለ. ያልተቀየረች (ያላመነች) ሴት ብዙውን ጊዜ ማንን ለመሳብ ትሞክራለች - እና ምን መዘዝ ያስከትላል? ምሳሌ 7:6፣ 7፣ 10፣ 18፣ 19፤ 2ኛ ነገሥት 9:3፤ ኢሳይያስ 3:16-26
“ፈታኝ የሆኑ ሴቶችም ይኖራሉ፣ እናም የወንዶችን ትኩረት ወደ ራሳቸው ለመሳብ እና ለማሸነፍ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ።”— The Review and Herald, May 17, 1887.
“የታይታ፣ ከልክ ያለፈ አለባበስ ብዙውን ጊዜ በለበሰው ሰዉ ልብ ውስጥ ምኞትን ያበረታታል እና በተመልካቹ ልብ ውስጥ ተራ ፍላጎቶችን ያነቃቃል። አምላክ፣ ከባህሪይ መበላሸት አስቀድሞ ብዙውን ጊዜ ኩራትና ከንቱ ልብስ አለባበስ እንደሚቀድም ይመለከታል።”— Child Guidance, p. 416.
ሐ. አብዛኞቹ ክርስቲያን ሴቶች አውቀው ወንዶችን ወደ ምንዝር ለመማረክ ባይፈልጉም ሁሉም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው በምን ዓይነት ኩራት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:3፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:9
“ለአንቺም (ለባልሽም) እንደ ኩራትሽ ትልቅ እንቅፋት የሆነ ነገር የለም። ሁለታችሁም ታይታ ትወዳላችሁ፤ ግን ይህ መልካም በሆነ ትሑት ሃይማኖት ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም።”— Testimonies for the Church, vol. 2, p. 493.
“መጽሐፍ ቅዱስ በአለባበስ ልከኝነትን ያስተምራል። . . . ይህ በአለባበስ፣ ቀለም የበዛባቸዉን፣ ጌጣጌጦችን ማብዛትን ይከለክላል። ወደ ለበሰው ሰዉ ትኩረት ለመሳብ ወይም ለማድነቅ ተብሎ የተነደፈ ማንኛውም መሣሪያ የአምላክ ቃል ካዘዘው ልከኛ ልብስ የተለየ ነው።
“በአለባበስ ራስን መካድ የክርስቲያናዊ ግዴታችን አካል ነው። በግልጽ ለመልበስ እና ከማንኛውም ዓይነት ጌጣጌጥና ብልጭልጭ መራቅ ከእምነታችን ጋር የሚስማማ ነገር ነው።”— Child Guidance, p. 423.
ረቡዕ
ግንቦት 07
4. የባል ግዴታ
ሀ. ጴጥሮስ ሚስቶችን ከተማጸነ በኋላ ለባሎች ምን ከባድ ምክር ነግሯቸዋል? ይህን ምክር ችላ ማለታቸው የሚያስከትለውን መንፈሳዊ ውጤትስ? 1ኛ ጴጥሮስ 3፡7
“ባል ሚስቱን በርኅራኄና በማይቋረጥ ፍቅር ይርዳት። በቤት ውስጥ እንደ ፀሀይ ጮራ እንድትሆን ቆንጆና አስደሳች ሊያደርጋት ከፈለገ ሸክሟን እንድትሸከም ያግዛት። የእርሱ ደግነትና ፍቅራዊ ጨዋነት ለእሷ ውድ ማበረታቻ ይሆንላታል፤ የሚሰጣትም ደስታ ወደ ገዛ ልቡ ደስታና ሰላምን ያመጣል።”— The Adventist Home, p. 218.
ለ. ያልተለወጠ ባል የሚስቱን ሕይወት እንዴት የሚያሳዝን እንደሚያደርግ ምሳሌ ስጥ። 1ኛ ሳሙኤል 25:3፣ 14፣ 17፣ 23–25
“ባል ጨካኝ፣ በቃኝ የማይል፣ አድራጎትዋን የሚኮንንና የሚተች ከሆነ ፍቅርና አክብሮትዋን ጠብቆ ሊያቆይ አይችልም፤ ትዳርም የሚያስጠላ ይሆንባታል። ራሱን ተወዳጅ ለማድረግ ስለማይጥር ባልዋን አትወደውም። ባሎች ጥንቁቆች፣ ትኩረት ሰጪዎች፣ የማይዋዥቁ፣ ታማኞችና ሩህሩሆች መሆን ይጠበቅባቸዋል። ርኅራኄና ፍቅር ሊያንፀባርቁ ይገባቸዋል። ሁሉም ክርስቲያን ሊኖረው እንደሚገባ ባልየው የተከበረ ባህርይ፣ የልብ ንጽህናና ከፍ ከፍ ያለ አዕምሮ ያለው ከሆነ፣ ይህ ምግባሩ በትዳሩ ውስጥ የሚገለጽ ይሆናል…. ሚስቱ ብርቱና ጤናማ እንድትሆን ይጥራል። በቤት ውስጥ ሠላም የሰፈነበት ሁኔታ ለመፍጠርና የሚያጽናኑ ቃላትን ለመናገር ይተጋል።”—Ibid., p. 228.
ሐ. እውነተኛ ክርስቲያን ባል ለሚስቱ አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ ለማነሳሳት ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረው ይገባል? ኤፌሶን 5:25፣ 28፣ 33፤ ቆላስይስ 3፡19
“ባሎች ምሳሌውን ማጥናትና በኤፌሶን ላይ የተገለጸው ምልክት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ መጣር ይኖርባቸዋል። . . . ባል በቤተሰቡ ውስጥ እንደ አዳኙ መሆን አለበት። ሚስቱንና ልጆቹን ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚፈልግ ክቡር በሆነው፣ እግዚአብሔር በሰጠው ወንድነቱ ይቁምን? . . እያንዳንዱ ባልና አባት የክርስቶስን ቃል ለመረዳት በአንድ ወገን ብቻ ፣ ሚስት ለባሏ መገዛት ላይ ብቻ በማሰብ፣ ሳይሆን ነገር ግን በቀራንዮ መስቀል ብርሃን በቤተሰብ ክበብ የራሱን አቋም በማጥናት ይማር።”— Manuscript Releases, vol. 21, p. 216
ሐሙስ
ግንቦት 08
5. በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ “አለቃ” የለም።
ሀ. በባልና ሚስት መካከል ያለው ግንኙነት ምን ያህል መቀራረብ አለበት? ዘፍጥረት 2:23፣ 24፤ ማቴዎስ 19፡4-6
“ባልም ሆነ ሚስት የገዥነት ጥያቄ ማቅረብ የለባቸውም። በዚህ ጉዳይ ላይ እግዚአብሔር መመሪያ አስቀምጧል። ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያንን እንደሚንከባከብ ሁሉ ባል ሚስቱን ሊንከባከባት ይገባል። ሚስት በበኩልዋ ባልዋን ልታከብርና ልታፈቅረው ይገባታል። በፍጹም ቁርጠኝነት አንዳቸው ሌላኛውን ፈጽሞ ላለማሳዘንና ላለመጉዳት የሚችሉትን ሁሉ የደግነት መንፈስ ማጎልበት አለባቸው።”— The Adventist Home, pp. 106, 107.
“በቤታችን ስምምነት እንዲሰፍን ከፈለግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ላይ ሊኖር ግድ ነው። ሚስት የክርስቶስ መንፈስ ካላት ለምትናገረው ትጠነቀቃለች፤ የተሰጠችም ትሆናለች፤ ሆኖም የባልዋ አጋር እንጂ ያለ ደሞዝ የምትሠራ ባሪያ እንደሆነች አይሰማትም። ባል የእግዚአብሔር አገልጋይ ከሆነ በሚስቱ ላይ ፈላጭ-ቆራጭነቱን የሚጭንባት አይሆንም። ከመጠን ባለፈ ጥንቃቄ የቤትን ፍቅር መጠበቅ አንችልም፤ የጌታ መንፈስ የሚኖርበት ከሆነ ግን የሰማይ አምሳል ይሆናል…. አንዱ ሲያጠፋ ሌላኛው የክርስቶስን ዓይነት ይቅር-ባይነት ያሳያል እንጂ በቀዝቃዛ መንፈስ አይርቅም።
ሚስትም ሆነች ባል የፈላጭ-ቆራጭነት ቁጥጥር በሌላኛው ላይ ለማስፈን መሞከር የለባቸውም። ለራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ትኩረት በመስጠት የራሳችሁ ሐሳብ የአጋራችሁን ስሜት እንዲያንበረክክ አታስገድዱ። በእንዲህ ዓይነት ስሜት ፍቅራችሁን እንደነበረ ማቆየት አትችሉም። ቸር፣ ትዕግስተኛና ይቅር-ባይ፣ አሳቢና ሩኅሩኅ ሁኑ። በጋብቻ መሐላችሁ ለመፈጸም ቃል እንደገባችሁ ብትተጉ በክርስቶስ ፀጋ ለእርስ በእርሳችሁ ደስታ በመፍጠር ውጤታማ ትሆናላችሁ።”—Ibid., p. 118.
አርብ
ግንቦት 09
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. ለትዳር ጓደኛዬ ያለኝ አመለካከትና የድምፅ ቃና አምላክ በግልጽ የመራቸውን መሠረታዊ ሥርዓቶች በተከታታይ ሊያንጸባርቅ የሚችለው እንዴት ነው?
2. ስህተቶቼን አምኜ ከባለቤቴ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈጣን መሆን ያለብኝ ለምንድነዉ?
3. ለምንድነው ለትዳር ጓደኛዬ ለመሞት ዝግጁ/ፍቃደኛ እንድሆን እግዚአብሔር የሚጠራኝ?
4. በሀሳቤ ውስጥ በባለቤቴ ላይ ከመማገጥ መራቅ የምችለው እንዴት ነው?
5. እኔና ባለቤቴ በአለባበሳችን፣ በምግብ ማብሰል ችሎታችን ወይም እንደ ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቤት፣ ወዘተ ባሉ ንብረቶች በመኩራት ጥፋተኞች ልንሆን እንደምንችል በጸሎት መመርመራችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?