Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I)

 <<    >> 
1ኛ ትምህርት ሰንበት፣ መጋቢት 28፣ 2016

የየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ

መታሰቢያ ጥቅስ፡- “ጌታም። ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።” ሉቃስ 22:31፣ 32

“ጴጥሮስ ራሱን እንድክድና ሙሉ በሙሉ በመለኮታዊ ኃይል ላይ እንዲታመን ከተመራ በኋላ ነበር፣ የበታች እረኛ ሆኖ እንዲያገለግል ጥሪውን የተቀበለው። . . . አንድ አማኝ ድክመቱን እስካላወቀ ድረስ በክርስቶስ ላይ መታመን እንደሚያስፈልገው ሊያውቅ አይችልም።”—የሐዋርያት ሥራ ገጽ. 515.

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   The Desire of Ages, pp. 244–251. 

እሁድ መጋቢት 22

1. ለክርስቶስ ጥሪ ምላሽ መስጠት

ሀ. ስምዖን ጴጥሮስ ከየሱስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘበትን ጊዜ ግለጽ። ዮሐንስ 1፡40-42

“እንድርያስ በልቡ የተሞላውን ደስታ ለመካፈል ፈለገ። ወንድሙን ስምዖንን ለመፈለግ ሄዶ ድምጹን ከፍ አድርገው 'መሲሑን አግኝተናል' አለ። ስመኦን ምንም ሁለተኛ ቅስቀሳ አልጠበቀም። እርሱ ደግሞ የመጥምቁ ዮሐንስን ስብከት ሰምቶ ነበርና አዳኙን ለማግኘት ቸኮለ። ባህሪውን እና የህይወት ታሪኩን የሚያነበዉ የክርስቶስ አይኖች በእርሱ ላይ አረፉ። ግልፍተኛ ተፈጥሮው፣ አፍቃሪና አዛኝ ልቡ፣ ፍላጎቱና በራስ መተማመኑ፣ የውድቀቱ ታሪክ፣ ንስሃ መግባቱ፣ ድካሙ እና የሰማዕትነት ሞት—አዳኙ ሁሉንም አንብቧል።”— The Desire of Ages, p. 139.

ለ. የሱስ ጴጥሮስንና ወንድሙን ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ በይፋ የጠራቸው በምን ሁኔታዎች ውስጥ ነው? ማቴዎስ 4:18-20

“የእነዚህ ሰዎች ፈጣን፣ ያለ ምንም የደመወዝ ቃል ሳይገባ፣ ያለ ምንም ጥያቄ መታዘዛቸው፣ አስደናቂ ይመስላል፤ ነገር ግን የክርስቶስ ቃላት አነቃቂ ኃይልን የተሸከሙ ግብዣዎች ነበሩ። ክርስቶስ እነዚህን ትሑት ዓሣ አጥማጆች ከርሱ ጋር ሆነዉ ሰዎችን ከሰይጣን እሥራት ነጻ የሚያወጡና አምላክን እንዲያገለግሉ የሚያደርጉ አደረጋቸዉ።”— Gospel Workers, p. 24.


ሰኞ መጋቢት 23

2. ቅን እና ቀናተኛ ደቀ መዝሙር

ሀ. ጴጥሮስ በደቀ መዝሙርነት መጀመሪያ ላይ ራሱን ያየው እንዴት ነበር? ሉቃስ 5፡8

“በክርስቶስ ዘመን የሕዝቡ ሃይማኖታዊ መሪዎች በመንፈሳዊ ሀብት የበለጸጉ እንደሆኑ ተሰምቷቸው ነበር። የፈሪሳዊው ጸሎት ‘አምላክ ሆይ፣ እንደሌሎች ሰዎች ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ’ (ሉቃስ 18፡11)፣ በከፍተኛ ደረጃ እራሱ የሚወክለዉን ክፍልንና የመላው አገሪቱን ስሜት ገልጿል። ነገር ግን የሱስን ከከበበው ሕዝብ መካከል መንፈሳዊ ድህነታቸውን የሚያውቁ ሰዎችም ነበሩ። ዓሣ ሲያሰግሩ በታየዉ ታላቅ ተዓምር የክርስቶስ መለኮታዊ ኃይል ሲገለጥ፣ ጴጥሮስ በአዳኙ እግር ስር ወድቆ፣ ‘ከእኔ ራቅ፤ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ሰው ነኝና' (ሉቃስ 5: 8) ብሎ ነበር፤ ስለዚህ በተራራው ላይ በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል በክርስቶስ ንጽሕና ፊት ‘ምስኪን፣ ረዳት አልባ፣ ድሆች፣ ዕውሮችና ራቁትነታቸው’ የሚሰማቸው ነፍሳት ነበሩ (ራእይ 3:17)።”— Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 6, 7.

ለ. ጴጥሮስ ስለ የሱስ ማንነት ምን ያምን ነበር? ማቴዎስ 16፡13-16

“ከመጀመሪያው ጀምሮ ጴጥሮስ የሱስ መሲሕ እንደሆነ ያምን ነበር። በመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት የተመለሱና ክርስቶስን የተቀበሉ ብዙ ሰዎች አሁን እርሱ ታስሮ ሲገደል፤ የእርሱን ተልእኮ መጠራጠር ጀመሩ ደግሞ አሁን የሱስ መሲህ መሆኑን ተጠራጠሩ። . . . የሱስ በዳዊት ዙፋን ላይ እንዲቀመጥ አጥብቀው ሲጠብቁ ከነበሩት ብዙዎቹ ደቀ መዛሙርት እርሱ እንደዚህ ያለ ሐሳብ እንደሌለው ሲረዱ ትተውት ሄዱ። ጴጥሮስና ጓደኞቹ ግን ከታማኝነታቸው ወደኋላ አላሉም። ትላንትና ያወደሱ እና ዛሬ ደግሞ የሚያወግዙ ሰዎች የመናናቅ አካሄድ የእውነተኛውን አዳኝ ተከታዮችን እምነት አላጠፋም። ጴጥሮስ ‘አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ሲል ተናግሯል። ንጉሣዊ ክብርን ጌታው እስኪያገኝ አልጠበቀም ነገር ግን በውርደቱ ተቀበለው። . . .

“የሱስም ለጴጥሮስ መልሶ፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብጹህ ነህ አለዉ።

“ጴጥሮስ የተናገረው እውነት የእያንዳንዱ አማኝ እምነት መሠረት ነው። ክርስቶስ ራሱ የዘላለም ሕይወት መሆኑን ያወጀው ራሱ ነው። ነገር ግን የዚህ እውቀት ባለቤት መሆን ራስን ለማክበር ምክንያት አይሆንም። ይህ በራሱ ጥበብ ወይም በጎነት ለጴጥሮስ አልተገለጠለትም። መቼም የሰው ልጅ በራሱ የመለኮትን እውቀት ማግኘት አይችልም። . . . የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ሊገልጥልን የሚችለው የራሱ መንፈስ ብቻ ነው። . . . ጴጥሮስ የክርስቶስን ክብር ማወቁ ‘ከእግዚአብሔር እንደተማረ’ የሚያሳይ ማስረጃ ነው። — The Desire of Ages, pp. 411, 412.


ማክሰኞ መጋቢት 24

3. መልስ ለማግኘት ጉጉ

ሀ. የጴጥሮስን ጠያቂ አእምሮ የሚያሳዩት እና ተመሳሳይ አመለካከት በማዳበር እንዴት ማደግ እንደምንችል የሚያሳዩት የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ናቸው? ማቴዎስ 15:15፤ 18:21፤ 19:27፤ ማርቆስ 13:3፣ 4

“እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ማንኛውንም ሐሳብ፣ ስሜትና ምኞት የሚያበረታታ ሌላ ጥናት የለም። . . . እዚህ ያለውን ህይወት እንዴት ማሻሻል እንዳለብንና የወደፊቱን ህይወት እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል እንማራለን። የአዕምሮን ጥያቄዎችና የልብ መሻትን የሚያረካ ሌላ መጽሐፍ የለም። የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት በማግኘትና እርሱን በመስማት ሰዎች ከዝቅተኛው የድንቁርናና የውርደት ጥልቀት ተነስተው የእግዚአብሔር ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ። . . .

“መጽሐፍ ቅዱስ በማስተማር ኃይሉ አቻ የሌለው ነው። ተማሪዎች የራዕይ እውነቶችን እንዲገነዘቡ የሚያስገድድ ምንም ነገር ለሁሉም ፋኩልቲዎች ብርታትን አይሰጥም። አእምሮ ቀስ በቀስ እንዲያሰላስል በተፈቀደላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ጋር ራሱን ያስተካክላል። በተለመዱ ጉዳዮች ብቻ ከተጠመደ፣ ከታላላቅና ከፍ ያለ ጭብጦችን ላይ ማሰላሰልን ከተወ፣ ድንክና ደካማ ይሆናል። ከአስቸጋሪ ችግሮች ጋር ለመታገል ወይም አስፈላጊ እውነቶችን ለመረዳት፣ ፈፅሞ የማይፈለግ ከሆነ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የዕድገት ኃይሉን ሊያጣ ይችላል። . . .

“በእግዚአብሔር ቃል አእምሮ ለጥልቅ ሐሳብ፣ ከሁሉ ለላቀ ለአምላክ ምኞት ተገዢነትን ያገኛል።”— Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 24, 25.

አብዝተው ጠያቂዎች ለአሁኑና ለዘላለማዊ ጥቅማቸው የሚያረጋግጥላቸውን በክርስቶስ ትምህርት ቤት በደህና ይማሩ ይሆናል።”— An Appeal to Mothers, p. 32.

ለ. በመንፈሳዊ ርዕሶች ላይ መጠየቅ የሚበረታታ ቢሆንም (ዮሐንስ 5:39) ጤናማ የሰው ልጅ የማወቅ ጉጉት ገደብ የሚኖረው መቼ ነው? ዘዳግም 29፡29

“[ሰይጣን] ወደ መለኮታዊ ጥበብና ኃይል ምሥጢር ውስጥ ዘልቆ ለመግባት የማያቋርጥ የማወቅ ጉጉት፣ እረፍት የለሽ፣ የፍላጎት መንፈስን ለማነሳሳት ዘወትር ይፈልጋል። ብዙ ሰዎች አምላክ የናቃቸውን ነገሮች ለመመርመር በሚያደርጉት ጥረት እርሱ የገለጠውንና ለመዳን አስፈላጊ የሆኑትን እውነት ችላ ይላሉ።”— Patriarchs and Prophets, pp. 54, 55.

“ግርማውን የሸፈነበትን መጋረጃ በእብሪት ለማንሳት መሞከር የለብንም። . . . የኃይሉ መደበቂያ እንዳለ፣ በአስፈሪው ምሥጢርና ደመና መሸፈኑ የምሕረቱ ማረጋገጫ ነው። መለኮታዊውን መገኘት የሚሸፍነውን መጋረጃ ማንሳት ሞት ነውና።”— The Review and Herald, April 7, 1885


ረቡዕ መጋቢት 25

4. ትንሽ እምነት፣ ብዙ በራስ መተማመን

ሀ. ጴጥሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ካጋጠመው በእምነት የመመላለስ ልምድ ምን እንማራለን? ማቴዎስ 14፡28-31

“[ጴጥሮስ] ዓይኑን ወደ የሱስ ከፍ አድርጎ ቢመለከት ይሻለዉ ነበር፤ ነገር ግን የተናወጠውን ማዕበል ተመለከተ፣ እምነቱም ከሸፈበት።”— Testimonies for the Church, vol. 2, p. 273.

አዳኙን ማየትን የህይወቱ ዋና ጉዳይ ካላደረገ በቀር እና በእምነት የይገባኛል ጥያቄውን የመጠየቅ መብት የሆነውን መብት ካልተቀበለ በቀር ዓይኖቹን በየሱስ ላይ ሳይተክል ጴጥሮስ በውሃው ላይ ሊራመድ እንዳልቻለ ሁሉ ኃጢአተኛውም ሊድን አይችልም። አሁን፣ የየሱስን እንዳያዩ ሸፍኖ ሰዎችን ወደ ሰው እንዲመለከቱ ማድረግ የሰይጣን ቁርጠኛ ዓላማ ነው። . . . ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዓመታት ሰውን ስትመለከትና ከሰው ብዙ ስትጠብቅ ቆይታለች፤ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት ተስፋችን ያተኮረበትን የሱስን አትመለከትም።”—Testimonies to Ministers, p. 93.

ለ. ጴጥሮስ ከየሱስ ጋር በቆየ ቁጥር ራሱንና ከባድ ፈተናዎችን የመቋቋም ችሎታውን ከፍ አድርጎ የገመተው እንዴት ነው? ማቴዎስ 26፡33–35፣ 69–75

ለሰው ነፍስ እንደ ኩራትና ራስ ብቁነት በጣም አደገኛ ነገር የለም። ይህ ከኃጢአት ሁሉ የሚበልጥ ተስፋ የሌለውና የማይድን ነው።”— Christ’s Object Lessons, p. 154.

“ከደቀ መዛሙርቱ መካከል የአንዱም ታሪክ የክርስቶስን የማሰልጠኛ ዘዴን ከጴጥሮስ ታሪክ በተሻለ የሚያስረዳ የለም። ደፋር፣ ግልፍተኛ፣ እና በራሱ የሚተማመን፣ ለማስተዋልና እርምጃ ለመውሰድ ፈጣን፣ አጸፋን ለመመለስ ፈጣን ቢሆንም ይቅር ባይና ደግ፣ ጴጥሮስ ብዙ ጊዜ ተሳስቷል፣ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ተገስጿል። . . . በትዕግስት፣ በታላቅ ፍቅር፣ አዳኙ የጴጥሮስን በራስ መተማመኑን ለመፈተሽና ትህትናን፣ ታዛዥነትን እና እምነትን እንዲያስተምረው ቆራጥ ከሆነው ደቀ መዝሙሩ ጋር ብዙ ሠራ።

ነገር ግን ትምህርቱን የተማረው በከፊል ብቻ ነበር። ራስ ብቁነት ሙሉ በሙሉ ከእርሱ አልተነቀልም ነበር። . . .

“ለሁሉም የጴጥሮስ ተሞክሮ ትምህርት ነበረው። በራስ ለሚተማመን ፈተና ሽንፈቱ ነው። የክፋት ሥራ አሁንም ካልተተወ፣ ክርስቶስ መከላከል አይችልም። ይሁን እንጂ ማዕበሉ ጴጥሮስን ሊጥለው በተቃረበ ጊዜ የማዳን እጁ እንደ ተዘረጋ፣ ጥልቅ ውኃም በነፍሱ ላይ በተነሳ ጊዜ በፍቅሩ ለማዳን እጁን ዘረጋ።”— Education, pp. 88, 89.

ሐ. ለምንድነው የብዙ አመታት የቤተክርስትያን አባልነት ለበለጠ የእምነት ጥንካሬ ዋስትና የማይሆነው? ሮሜ 11፡20–22፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10:12፤ 8፡2።


ሐሙስ መጋቢት 26

5. የተለወጠ ሐዋርያ

ሀ. መጨረሻው በኃጢአትና በኀፍረት መዉደቅ እንደሆነ እያወቀ አምላክ የራሳችንን ጎዳና ከመከተል የማይከለክለው ለምንድን ነው? ኢሳይያስ 48:17ሉቃስ 22:31፣ 32

“ጴጥሮስ ክርስቶስን ከመካዱ በፊት፡- በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለው። ሉቃስ 22፡32። እነዚህ ቃላቶች ይህ ሐዋርያ ወደፊት ወደ እምነት መምጣት ለሚገባቸው ሰዎች ሊያደርገው ስላለው ሰፊና ውጤታማ ሥራ ጉልህ ድርሻ ነበራቸዉ። ለዚህ ሥራ፣ የጴጥሮስ የራሱ የኃጢአት፣ የፈተናና የንስሐ ልምድ እርሱን ለሥራዉ አዘጋጅቶታል። ድክመቱን እስካላወቀ ድረስ፣ የአማኙን በክርስቶስ ላይ የመደገፍን አስፈላጊነት ማወቅ አልቻለም። . . . አሁን ተለወጧልና ተቀባይነት አግኝቷል፣ . . . ክርስቶስ ለእርሱ እንዳደረገው ሁሉ ለእርሱም ለተሰጡት በጎችንና ጠቦቶችን በፍቅር ይይዛቸዋል።”— The Acts of the Apostles, pp. 515, 516.

ለ. በኋለኛው ዘመን፣ ያ የተለወጠው ጴጥሮስ ፈተና ውስጥ ላሉ አማኞች በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ምን ማበረታቻ ሰጥቷል? 1ኛ ጴጥሮስ 3:14፤ 4፡12–14።

“እነዚህ ደብዳቤዎች የክርስቶስን መከራ በእርሱም መጽናናቱን እንዲሁም ሰውነቱ ሁሉ በጸጋ የተለወጠና የዘላለም ሕይወት ተስፋው አስተማማኝና ጽኑ በሆነለት ሰው የተጻፉ መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው።”—Ibid., p. 517.


አርብ መጋቢት 27

የግል ግምገማ ጥያቄዎች

1. በተለያዩ የሕይወት ሁኔታዎች ውስጥ የየሱስን ድምፅ ስሰማ፣ ልክ እንደ ጴጥሮስ ፈጣን ምላሽ መስጠት የምችለው እንዴት ነው?

2. የክርስትና ሕይወት የዓመታት ብዛት እየጨመረ ሲሄድ ፣ ከቶ ምን መርሳት የለብኝም?

3. ዛሬ በማያቋርጥ ሁኔታ ትኩረት በሚከፋፍልበት ዘመን፣ ለዘለአለም መዳን በቁም ነገር ካሰብኩኝ የተፈጥሮ ጥያቄዬን ወዴት ማድረግ አለብኝ?

4. በየትኞቹ የሕይወት ዘርፎች ውስጥ በራስ የመተማመን እና የራስ ብቁነት አደጋ ሊያጋጥመኝ ይችላል?

5. ስሕተት ሲፈጽም፣ ከዚህ ልምድ እንዴት አወንታዊ ትምህርቶችን ማግኘት እችላለሁ?

 <<    >>